Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Monday, 05 March 2012 14:31

የግጥም ጥግ

Written by 
Rate this item
(5 votes)

ጥቁር ድል

በደም ላይ ስጋ ተቆርሶ

ከጐድን አጥንት ከስክሶ

ከኑሮም ነብስ ለግሶ

ከምድርም እሰማይ ደርሶ

ታሪኩን በወርቅ የፃፈ

ለትውልድ ዘር ያተረፈ

ገናናው እንደ ተራራ

ሣተናው እንደ ደመና

ታምኖልኝ እንደ ወይራ

ወረሰኝ የሱ ድል ዝና

ስስት አያውቅ እሱነቱ

እምነት ታጥቆ እስከ አንገቱ

ደም አቡክቶ ለምድሪቱ

ህይወት ሰጥቶ ለፍጥረቱ

በደሙ ታሪክ ያተመ

በአጥንቱ ሀውልት ያቆመ

ቁስለቱ ትውልድ ያከመ

በሞቱ ክብር የደገመ

ተራራ የወለደችው

ሸንተረር ያሣደገችው

ሰርግ አለው ደምቆ የከበረ

በአጀባ ገዝፎ ያማረ

ይህች ሀገር የወላድ ወላድ

ማህፀኗ ጀግና የሚያለምድ

ከአድዋ በፊትም ቀድሞ

ወዲህም ታሪክ ተደግሞ

ጀግኖቹ እልፍ አእላፋት

ተባዝተው ምድርን የሞሏት

ፋኖዬ የገደል ጉንዳን

በደረት ገፍቶ ሽቅቡን

ሠርግ አለው ደምቆ የከበረ

በአጀባ ገዝፎ ያማረ

በዋሻው ደሙ ተጠምቆ

አካሉን ሥጋ ሞሽልቆ

አጥንቱን ጐድን ሰንጥቆ

ነብሱን ዳረጐት መርቆ

ለድንግል ሙሽሪት ክብሯ

አቆማት ወድቆ ከስሯ

ለአድዋ ጀግኖች መታሰቢያ

የካቲት 2004

ከኢሳያስ ከበደ

 

 

Read 5570 times Last modified on Monday, 05 March 2012 14:35