Monday, 08 August 2016 05:31

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ለ33ኛ ጊዜ ተማሪዎቹን አስመረቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

    ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 798 ተማሪዎች የዛሬ ሳምንት በሚሊኒየም አዳራሽ አስመርቋል፡፡ በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የማዕድን ምህንድስና ተማሪዎችን ማስመረቁም በእለቱ ተገልፆል፡፡
 ዩኒቨርሲቲው በማስተርስ ኦፍ አድምኒስትሬሽን፣ በመጀመሪያ ዲግሪ ደግሞ በዴቨሎፕመንት ኢኮኖሚክስ፣ በቢዝነስ ኢኮኖሚክስ፣ በአካውንቲንግና ፋይናንስ፣ በማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሳይንስ፣ በኮምፒዩተር ሳይንስ፣ በአርክቴክቸር ኤንድ አርባን ፕላኒንግ፣ በሶሲዮሎጂና በሶሻል አንትሮፖሎጂ፣በክሊኒካል ነርሲንግና በሌሎችም ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች የሚድሮክ ሊቀመንበር ዶ/ር ሼህ መሀመድ አሊ አላሙዲንና የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ኦፊሰርና የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው በተገኙበት አስመርቋል፡፡ ዩኒቨርስቲው በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች የላቀ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማት ሰጥቷል፡፡ በሌላ በኩል፤በየአመቱ ከማህበረሰቡ ውስጥ በአርአያነት የሚመረጡ ግለሰቦችንም ይሸልማል፡፡
ዘንድሮም የቱሪዝም አባት ተብለው የሚጠሩት አቶ ሀብተስላሴ ታፈሰ፣ የማስታወቂያ ባለሙያው የትውልዱ አምባሳደር አቶ ውብሸት ወርቃለማሁና በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ፣ የዩኒቨርሲቲው አርክቴክቸርና ኸርባን ዴቨሎፕመንት መምህር  ዶ/ር ፈረደ በፍቃዱ የሊቀመንበሩን ዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ ከሼህ መሀመድ አሊ አላሙዲ እጅ ተቀብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ በደሴ ልዩ ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ከመቶ በላይ ተማሪዎች ዛሬ እንደሚያስመርቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 2645 times