Monday, 08 August 2016 05:20

ዜድቲኢ ለሶስተኛ ጊዜ በጉለሌ ከተማ ዛፍ ተከላ አካሄደ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   ዓለምአቀፉ የቴሌኮምና የኔትወርክ ኩባንያ ዜድቲኢ፤ ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ በጉለሌ ክ/ከተማ ከ2 ሺ በላይ ዛፎችን ተከለ፡፡ በዛፍ ተከላው ላይ በኢትዮጵያ የቻይና የንግድና ኢኮኖሚ አማካሪ  ወ/ሮ ሊዮ ዩን እና የዜድቲኢ ኢትዮጵያ ምክትል ዳይሬክተር ሚስተር ሊ ጉዋንግ ዮንግን ጨምሮ ከ200 በላይ የኩባንያው የውጭና የአገር ውስጥ ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡ ‹‹Green Action Tree Planting›› በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ የዛፍ ተከላ ላይ ምክትል ዳሬክተሩ ባደረጉት ንግግር፤ ዜድቲኢ ባለፉት 16 ዓመታት በቴሌኮም ማስፋፋት፣ በኔትወርክ ዝርጋታና በተለያዩ ማህበራዊና በጎ አድራጎት ስራዎች በመሳተፍ፣ የኢትዮጵያ መንግስት አጋር መሆኑን ጠቅሰው ባለፉት ሶስት አመታት የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ለመደገፍ የዘንድሮን ጨምሮ ከስድስት ሺህ በላይ ዛፎችን መትከሉን ገልፀዋል፡፡
 የቻይና ብሄራዊ ቀን በየአመቱ ማርች 12 እንደሚከበር ጠቁመው፣ የቻይና ህዝብ ተፈጥሮን ለመጠበቅ ዛፍ እንደሚተክል የተናገሩት ምክትል ዳሬክተሩ፤ይህ አይነት ተግባር በኢትዮጵያም ሊበረታታ እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡ የዛሬው የዛፍ ተከላ ቀን ለቻይናም ሆነ ለኢትዮጵያ ትርጉም ያለው ነው ያሉት አማካሪዋ፤ኢትዮጵያ በጣም ቆንጆ አገር እንደመሆኗ ውበቷንና ተፈጥሮዋን በመጠበቅ ይበልጥ እንድትዋብ፣ ዛፍ መትከልን ባህል ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

Read 865 times