Monday, 05 March 2012 13:52

“የጥበባት ጉባዔ” ለገበያ ቀረበ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው በለጠ “የጥበባት ጉባዔ” የተሰኘ ባለ 466 ገጽ መጽሐፍ ለንባብ አበቁ፡፡ በአስቴር ነጋ አሳታሚ ድርጅት የቀረበው መጽሐፍ በኢትዮጵያ 75 ብር ከኢትዮጵያ ውጪ ደግሞ በ50 ዶላር እየተሸጠ ነው፡፡ በቋንቋ ሰብአዊ ገጽታ ላይ ያተኮረው መጽሐፍ ለደራሲው አምስተኛ ሥራቸው ሲሆን ካሁን ቀደም በስማቸው፣ እንዲሁም “ዳኘው” እና “ዳግላስ ጴጥሮስ” በተሰኙ የብዕር ሥሞች ከ882 በላይ ሂሳዊ ጽሑፎች በኢትዮጵያ ሬዲዮ፣ በአዲስ ዘመን እና የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ፤ በየካቲት መጽሔትና በሌሎች የመገናኛ ብዙሃን አቅርበዋል፡፡ በደራሲነት፣ በአርታዒነትና በሃያሲነት የሚታወቁት አቶ ጌታቸው፤ በኢትዮጵያ ሬዲዮ ከመፃሕፍት ዓለም ፕሮግራም ይሰጧቸው በነበሩ ሂሳዊ አስተያየቶችም የሚታወቁ ሲሆን በቅርቡ ለሕትመት በበቃው “የዳግማዊ ምኒሊክ ደብዳቤዎች” መጽሐፍ ላይ በአርታኢነት ሰርተዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የአስቴር ነጋ አሳታሚ ድርጅት ኦፕሬሽን ማናጀር የሆኑት ደራሲና ሃያሲ ጌታቸው በለጠ “መንትዮች”፣ “ስሞተኛው”፣ “የአመራር ጥበብ”፣ “ኤሎሄ እና ሃሌሉያ” የተባሉ መፃሕፍትን በግል ሲያሳትሙ “የዘመን ቀለማት” የተሰኘ መጽሐፍን ደግሞ በጋራ አበርክተዋል፡፡

 

 

Read 1353 times Last modified on Monday, 05 March 2012 13:53