Monday, 05 March 2012 13:49

“ሙዚቃል” ሐሙስ ይመረቃል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በገጣሚ ኤፍሬም ስዩም የተዘጋጀውና ቮካል ሬከርድስ ያሳተመው የገጣሚ ኤፍሬም ስዩም “ሙዚቃል” የግጥም ሲዲ በተለምዶ ቺቺንያ በሚባለው አካባቢ በሚገኘው H2O ክለብ በመጪው ሃሙስ ምሽት ይመረቃል፡፡ ሙሉ የሙዚቃ ቡድን በመጠቀም በተዘጋጀው የሲዲ ግጥም ላይ ዶር. ሔራን ሠረቀብርሃን፣ አበጋዙ ክብረወርክ ሺዎታ፣ ሄኖክ ተመስገን፣ ጆርጋ መስፍን፣ ግርማ ይፍራሸዋ እና ሌሎችም በሙዚቃ ተሳትፈውበታል፡፡

የሐሙሱን ምርቃት ያዘጋጀው H2O ክለብ ኃላፊዎች ክለብ ከማስጨፈር ውጪ ሌላ የሚሠራ የማይመስላቸው ስላሉ ያንን መቀየር እንፈልጋለን በማለት በምሽት ክበባቸው ሌሎች የኪነጥበብ ሥራዎችን በኤፍሬም ስዩም ግጥሞች ማቅረብ እንደሚጀምሩና መጨፈር ብቻ እፈልጋለሁ ለሚሉም እንደሚታሰብበት እንዲሁም በኪነጥበብ ዝግጅቶች ከኪነጥበብ ውጪ ያሉ ሰዎችንም በመጋበዝ ጥበቡን ለማነቃቃት እንደታቀደ ጠቁመዋል፡፡

 

 

Read 1144 times Last modified on Monday, 05 March 2012 13:50