Monday, 05 March 2012 13:46

“ከአድማስ ፊት” ነገ በሻሸመኔ ይቀርባል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

“ስብሐት ገብረእግዚአብሔር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይዘከራል”

በሻሸመኔ ከተማ ኪነጥበብ አፍቃሪዎች የተቋቋመው “ከአድማስ ፊት” የኪነጥበብ ማህበር ነገ ከሰዓት በኋላ በሻሸመኔ ሁለገብ አዳራሽ የጥበብ ዝግጅቱን ያቀርባል፡፡ አርቲስት ጥላሁን ዘውገና አርቲስት አለልኝ መኳንንት የክብር እንግዶች ሲሆኑ ባለፈው ሳምንት ሕይወቱ ያለፈውና የዝግጅቱ የአንድ ወቅት እንግዳ የነበረው መምህር፣ ጋዜጠኛ፣ አርታዒና ደራሲና ስብሐት ገብረእግዚአብሔር እንደሚዘከር ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዝግጅቱ ላይ ግጥሞች፣ ባህላዊ ውዝዋዜና ሌሎች ዝግጅቶች የሚኖሩ ሲሆን የሐዋሳው “60ሻማ” አባላት በተጋባዥነት የጥበብ ሥራዎችን እንደሚያቀርቡ ተጠቁሟል፡፡

በሌላም በኩል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ባለፈው ሳምንት በሞት ከዚህ አለም የተለየውን አንጋፋውን ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ ተርጓሚ፣ ሃያሲ ገጣሚ ስብሃት ገብረእግዚሐብኤር ስራዎችን ለመዘከር ውይይት አዘጋጀ፡፡ ማክሰኞ በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ (ስድስት ኪሎ ካምፓስ) ራስ መኮንን አዳራሽ ውይይቱ ይካሄዳል ውይይቱ፡፡ በዝግጅቱ በኢትዮጵያ ሥነፅሑፍ ትልቅ አስተዋፅኦ ያላቸው ምሁራን ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በሌላም በኩል የዩኒቨርሲቲው የያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት የቻይናው ኮሙኒኬሽን ኩባንያ ሀዋዌ በርካታ መፃሕፍትና ፒያኖዎች እንደረዳው አስታወቀ፡፡

 

 

Read 1034 times Last modified on Monday, 05 March 2012 13:49