Monday, 25 July 2016 09:13

“ዘ ግሬት ካቨር ሂት” የሙዚቃ ኮንሰርት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በበርካታ የአለም ቋንቋዎች የሚያቀነቅነውና አክሱም ተወልዶ፣ አስመራ ያደገው ድምፃዊ ቴዎድሮስ
አትክልት ‹‹The Great Cover Hit›› የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት በመጪው ሀምሌ 30 ከምሽቱ 2፡
00 ጀምሮ በጌትፋም ሆቴል እንደሚያቀርብ ተገለፀ፡፡ በፈረንሳይኛ፣ በጣሊያንኛ፣ በጀርመንኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በአረብኛና ሌሎች ቋንቋዎች ያቀነቅናል የተባለው ድምፃዊው ያለምንም እረፍት በኢትዮ ኖታ ታጅቦ ለ4 ሰዓት ታዳሚውን ያዝናናል ተብሏል፡፡ በሙዚቃዎቹ
ስለ አ ንድነት፤ ስ ለ ሰ ላም ስ ለፍቅር እ ንደሚያቀነቅንና በተለይም የኤርትራና የኢትዮጵያ መለያየት ጉዳይ እንደሚያንገበግበው ገልጿል፡፡ በኮንስርቱ ላይ ለመታደም ለቪአይፒ አንድ ሺህ ብር ሲሆን ለመደበኛ 500 ነው ተብሏል፡፡ የኮንሰርቱ መታሰቢያነት ለእውቁ ድምፃዊ ተክሌ ተስፋዝጊ እንደሆነም ታውቋል፡፡

Read 2212 times