Print this page
Monday, 05 March 2012 13:34

ከአሜሪካ ውጪ የተሰሩ ፊልሞች ኦስካር ቀንቶአቸዋል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የኦስካር ሽልማት ስነስርዓት ከአሜሪካ ውጭ የተሰሩ ፊልሞች ዋና ዋናዎቹን ሽልማቶች እንደወሰዱ ሎስ አንጀለስ ታይምስ ገለፀ፡፡ የፈረንሳይ፤ የፓኪስታን፤ የኢራንና የኳታር የፊልም ባለሙያዎችና ፊልም ሰሪዎች የኦስካር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ በፈረንሳይ የፊልም ባለሙያዎች የተሰራው ድምፅ አልባው ፊልም “ዘ አርቲስት” አምስት ዋና ዋና ሽልማቶች መውሰዱ ለፈረንሳይ ሲኒማ መነቃቃትን ይፈጥራል ተብሏል፡፡ የማርቲን ስኮርሴሲ ‹ሁጎ› ዋና ዋና ሽልማቶችን ባያሸንፍም ከታጨባቸው 11 ዘርፎች አምስቱን ለመሸለም በቅቷል፡፡ “ዘ አርቲስት” የዓመቱ ምርጥ ፊልም ሆኖ ኦስካር ሲሸለም ፈረንሳዊው ፈረንሳዊያኑ የፊልሙ መሪ ተዋናይ ጂን ጁንድሪንና ዲያሬክተሩ ማይክል ሃዛናፊከስ በምርጥ ተዋናይና በምርጥ ዲያሬክተርነት ኦስካር ወስደዋል፡፡ በሌሎች የሽልማት ዘርፎች በፓኪስታናዊቷ ዲያሬክተር አባይድ ችኖይ የተሰራው “ሴቪንግ ፌስ” ምርጥ ዶክመንታሪ ሲባል የኢራኑ ፊልም “ኤ ሴፓሬሽን” በውጭ ቋንቋ የተሰራ የዓመቱ ምርጥ ፊልም ተብሎ የኦስካር ክብርን ተቀዳጅተዋል፡፡

በምርጥ ሴት ረዳት ተዋናይት ዘርፍ ያሸነፈችው ጥቁር አሜሪካዊቷ ኦክታቪያ ፔንሰር ስትሆን የተወነችበትን “ዘ ሄልፕ” የተባለ ፊልም ፕሮድዩስ በማድረግ የአቡዳቢው ኢሜጅ ኔሽን ኩባንያ እንደተሳተፈበትም ታውቋል፡፡ ምርጥ ተዋናይት ተብላ ኦስካርን ለ3ኛ ጊዜ የወሰደችው በ”አይረን ሌዲ” ማርጋሬት ታቸርን የተወነችው ሜሪል ስትሪፕ ስትሆን በ”ዘ ቢግነርስ” ፊልም ላይ በረዳት ተዋናይነት የሰራው የ82 ዓመቱ ክሪስቶፈር ፕላመር ኦስካርን በመሸለም በእድሜ አንጋፋው ተዋናይ ሆኗል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ለእይታ ከበቃ 14 ሳምንት ያሳለፈው “ዘ አርቲስት” ፊልም 76.5 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያስመዘገበ ሲሆን ከኦስካር ምሽት በኋላ ገበያው እንደሚደራለት ታውቋል፡፡ በ15 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተሰራው ፊልሙ በቀጣይ ሳምንታት ገቢው እስከ 100 ሚሊዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል፡፡

 

 

 

Read 1540 times Last modified on Monday, 05 March 2012 13:37