Monday, 05 March 2012 13:28

በ”ኔቪ ሲልስ” ወታደሮች የተሰራው ፊልም ገበያውን ይመራል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

በአሜሪካ ልዩ የባህር ሃይል ወታደሮች “ኔቪ ሲልስ” የተተወነው “አክት ኦፍ ቫሎር” የተሰኘው ፊልም 24.7 ሚሊዮን ዶላር ሳምንታዊ ገቢ በማስመዝገብ ቦክስ ኦፊስን መምራት ጀመረ፡፡ በእውነተኛ የአሜሪካ ባህር ሃይል ወታደሮች ላይ ተመስርቶ ለቀረፃው 13 ሚሊየን ለማስተዋወቅ 30 ሚሊየን ዶላር የወጣበት የተሰራው ፊልም በ12 ሚሊዮን ዶላር ነው የተገዛው፡፡ በኦስካር ሰሞን በሰሜን አሜሪካ በ2200 ሲኒማ ቤቶች ለመታየት የበቃም ብቸኛ አዲስ ፊልም ነው፡፡

“ዘ አክት ኦፍ ቫሎር” በአሜሪካ ባህር ሃይል ሙሉ ድጋፍ መሰራቱን ያመለከተው ሮይተርስ፤ ፊልሙ በአሜሪካ የባህር ሃይል ወታደሮች ገድል ዙሪያ በሆሊውድ የሚሰሩ የልቦለድ ፊልሞችን ለማሳጣት የተሰራ ነው መባሉን ጠቅሷል፡፡

 

Read 1005 times Last modified on Monday, 05 March 2012 13:33