“ዘ ዲክታተር› ሳቻ ባሮን በአሜሪካ የሰራው 3ኛው የኮሜዲ ፊልሙ መሆኑን የገለፀው ዘ ሆሊውድ ሪፖርተር በዓለማችን አምባገነን መሪዎች ላይ ሰፊ ትችት እንደሚታይበት ጠቁሟል፡፡ የሳቻ ባሮን በአሜሪካ የተሰራ የመጀመርያ ፊልም በርእሱ ረጅምነት የሚታወቀው‹ ካልቸራል ለርኒንግ ኦፍ አሜሪካ ፎር ሜክ ቤነፊት ግሎርየስ ኔሽን ኦፍ ካዛኪስታን” ሲሆን በ18 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተሰርቶ 280 ሚሊዮን ዶላር በመላው ዓለም ገቢ ሆኖበታል፡፡ ከወር በኋላ የሚታየው ዘ ዲክታተር በቀድሞው የኢራቅ መሪ ሳዳም ሁሴን በተፃፈው “ዘቢባህ ኤንድ ዘ ኪንግ” የተባለ መፅሃፍን በመንተራስ ተሰርቷል፡፡ በፊልሙ ላይ በመሪ ተዋናይነት ለሰራው ሳቻ ባሮን 20 ሚሊዮን ዶላር ተከፍሏል ያለው “ዘ ሆሊውድ ሪፖርተር” የኮሜድያኑ ክፍያ የሆሊውድ ትልቅ ተከፋዮቹ ቶም ክሩዝና ጆኒ ዲፕ መቀራረቡ አስገራሚ ነው ብሏል፡፡