Print this page
Monday, 05 March 2012 13:11

ዊዝ ካሊፋ ዘንድሮ 100 ሚ ዶላር አገኛለሁ አለ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

50 ሴንት ለአፍሪካ ረሃብ እየሰራ ነው

የ24 ዓመቱ ራፕር ዊዝ ካሊፋ ዘንድሮ 100 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደሚያገኝ መግለፁን ፎርብስ መፅሄት አስታወቀ፡፡ በአጭር ጊዜ የተሳካለት ራፐር የተባለው ዊዝ ካሊፋ ከ10 ሚሊዮን በላይ በዓመት ገቢ ከሚኖራቸው ራፐር መግባትም ያጠያይቃል ብሏል ፎርብስ ራፐሩ በቅርቡ ለገበያ የሚያበቃው የምርጥ ሙዚቃዎቹ ሚክስ አልበም እና በብዙ ቦታዎች የሚያቀርባቸው ኮንሰርቶች ስኬታማነት ዊዝ ካሊፋ በሙሉ ስሙ ካሜሮን ጂብሪል ቶማዝ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ከ2005 ጀምሮ አራት አልበሞችን ለገበያ ያበቃና የመጨረሻ አልበሙ ዘንድሮ ለገበያ የቀረበው ኦ.ኤን.አይ.ኤፍ.ሲ የተባለ ነው፡፡

ከወር በፊት በበጎ ፈቃድ ስራ በኬንያ በሶማሊያና የሚገኙ የሶማሊያ ስደተኞች ካምፖችን የጎበኘው ፊፍቲ  ሴንት፤ የአፍሪካ ጉዞው አዲስ አልበም ለመስራት የሚያነቃቁ ግጥሞችን እንዳፃፈው ለአሶሽዬትድ ፕሬስ ተናገረ፡፡ ራፐሩ በተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሚካሄደውና “የአፍሪካን ረሃብ እናቁም” የሚለውን ዘመቻ በመደገፍ ለ3.5 ሚሊዮን ተረጂዎች የሚሆን ምግብ መለገሱ ታውቋል፡፡

 

 

 

Read 1217 times Last modified on Monday, 05 March 2012 13:18