Saturday, 28 May 2016 15:06

ዶ/ር ቴዎድሮስ ከቀናቸው፣ የ600ሺ ብር ደሞዝተኛ ይሆናሉ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(35 votes)

ከኢትዮጵያ መንግስት በፊት፣ 31 አገራት ለዶ/ር ቴዎድሮስ ድጋፍ ሰጥተዋል

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፤ ከአመት በኋላ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ለመሆን በምርጫ ካሸነፉ፣ በተባበሩት መንግስታት ውስጥ ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ የያዙ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ይሆናሉ፡፡
ለዓለም ጤና ድርጅት መሪነት ድጋፍ ሲያሰባስቡ የቆዩት ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ ከ31 የአፍሪካ ሀገራት ድጋፍ እንዳገኙ መረጃዎች አረጋግጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ድጋፉን የገለፀው፣ ገና በዚህ ሳምንት እንደሆነም፣ ምንጮች ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
ዶ/ር ቴዎድሮስን ጨምሮ አምስት ሰዎች በየፊናቸው ድጋፍ ለማግኘት ሲጣጣሩ የቆዩ ቢሆንም በመጪው ሐምሌ ወር ለሚካሄደው ምርጫ በተወዳዳሪነት የሚቀርቡት ግን ሶስት እጩዎች ብቻ ናቸው፡፡ የአለም አገራት በሚሰጡት ድምጽ ቀዳሚውን ደረጃ ያገኘ ተወዳዳሪ፣ የአለም ጤና ድርጅት ዳሬክተር ይሆናል፡፡ ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሸነፉ፣ የመጀመሪያው አፍሪካዊ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ይሆናሉ ተብሏል፡፡ የዳሬክተሩ የወር ደሞዝ 31ሺ ዶላር ገደማ ነው (ከ600ሺ ብር በላይ)፡፡


Read 6398 times