Saturday, 21 May 2016 16:38

“ዘሔርሙ” ዛሬ፤“መዋዕለ ስደት” ነገ ይመረቃሉ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

    በደራሲ ፍቅረ ተክለማርያም የተፃፈው “ዘሔርሙ” የተሰኘ መፅሐፍ በዛሬው ዕለት ከቀኑ 8፡00 -11፡00 በብሔራዊ ቤተ-መፃህፍትናቤተ-መዛግብት አዳራሽ ይመረቃል፡፡ ደራሲው“መግባቢያ” በሚል ርዕስ ባሰፈረው ማስታወሻ ስለ
ጽሁፉ ዘውግ ሲገልጽ፤ “ልቦለድም አ ልላችሁ!…ኢ-ልቦለድም አልላችሁ! አንብባችሁ ስትጨርሱ
በራሳችሁ ፈርጁት” ብሏል፡፡ መፅሐፉ በ226 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን ለአገር ውስጥ በ60 ብር ከ70 ሳንቲም፣ ለውጭ አገራት በ20 ዶላር ለገበያ መቅረቡን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ በእቴቱ ገመቹ የተጻፈውና የስደትን አስከፊ ሁኔታና የሚያስከትለውን መዘዝ የሚያስቃኘው “መዋዕለ ስደት” የተሰኘ መፅሐፍ በነገው ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ በቅርስ ጥናት ጥበቃ ባለሥልጣን አዳራሽ ይመረቃል፡፡ ፀሐፊዋ ከረዥም የእግር ጉዞ፣ በተለይም ከግብፁ የሲናይ በረሃ መቃጠል በኋላ እስራኤል ገብታ በስደት የቀመሰችውን እስራትና ስቃይ በመፅሃፍዋ እንደተረከችው ታውቋል፡፡ በ165 ገፆች የተዘጋጀው መፅሀፉ፤ በ45 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 1142 times