Saturday, 30 April 2016 11:15

የጋምቤላ ክልል የቀድሞ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ 7 ሰዎች በእስራት ተቀጡ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(9 votes)

ክልሉን ከፌደሬሽኑ ለመገንጠል ተንቀሳቅሰዋል ተብሏል  
   የጋምቤላን ክልል ከፌደሬሽኑ በኃይል ለመገንጠል ሙከራ አድርገዋል የተባሉት የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ 7 ግለሰቦች ከ7 ዓመት እስከ 9 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው፡፡
የክልሉ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ ኦኳይ፤ ከዚህ በፊት በምንም ወንጀል ተከሰው እንደማያውቁ፣ ከ1978 እስከ 1992 ለ13 ዓመታት በጤና ቢሮ የተለያዩ ኃላፊነቶች ማገልገላቸውንና ክልሉን በፕሬዚዳንትነት መምራታቸውን በመግለፅ የቅጣት ማቅለያ ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ በ9 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል፡፡  በተመሳሳይ ዴቪድ ኡጁሉ የንቅናቄው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ሆነው በድርጊቱ ከፍተኛ ተሳትፎ እንደነበራቸው በመረጋገጡ ፍ/ቤቱ በ9 ዓመት እስራት ይቀጡ ብሏል፡፡
ቀሪዎቹ ኦታካ ኡዋራ፣ ኡማንኤው፣ ኦቦንግ አሞኮ፣ ኡጁሉ ቻም እና ኦቻን ኦፒዮ በንቅናቄው ውስጥ በአባልነት በመሳተፋቸውና የቡድኑን አላማ አውቀው ወታደራዊ ስልጠና በመውሰድ ጥቃት ለመፈፀም በዝግጅት ላይ ስለነበሩ፣ በ7 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል፡፡   

Read 3276 times