Saturday, 23 April 2016 10:46

ፊደል ካስትሮ መሞቻዬ ደርሷል አሉ

Written by 
Rate this item
(4 votes)

 - ወንድማቸው ራኡል ካስትሮ በኮሙኒስት ፓርቲ መሪነቱ ይቀጥላል

    ኩባን በመምራት ላይ የሚገኘው ወንድማቸው ራኡል ካስትሮ በኮሙኒስት ፓርቲ መሪነቱ እንደሚቀጥል ባለፈው ማክሰኞ መገለጹን ተከትሎ፣ የቀድሞው የአገሪቱ አብዮታዊ መሪ ፊደል ካስትሮ፣ ለፓርቲው አባላት ባደረጉት ንግግር፣ መሞቻዬ ደርሷል፣ ተግታችሁ የኔን ሃሳቦች ተግባራዊ ማድረጋችሁን ቀጥሉ ሲሉ መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘገበ፡፡
ለአመታት ከአደባባይ ርቀው የቆዩት ካስትሮ ለፓርቲያቸው አባላት ባደረጉት ንግግር፣ በቅርቡ 90 አመት ይሞላኛል፤ ወደማይቀርበት ሞት የምሄድበት ጊዜም ተቃርቧል፤ እንግዲህ በርቱና የኩባን ኮሙኒስቶች ሃሳቦች ህያው ሆነው እንዲቀጥሉ የተቻላችሁን ሁሉ አድርጉ ብለዋል፡፡
ከ55 አመታት በፊት አንስቶ አገሪቱን በመምራት ላይ የሚገኘውን የኩባ ኮሙኒስት ፓርቲ ያቋቋሙት ፊደል ካስትሮ ባጋጠማቸው የጤና እክል  በ2008 ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን ያስታወሰው ዘገባው፣ ፊደል ካስትሮ ያደረጉት ንግግር ፓርቲው በአዲሱ ትውልድም ከስልጣኑ እንዳይለቅ ለማሳሰብ የታለመ ነው መባሉንም ገልጧል፡፡

Read 2420 times