Saturday, 25 February 2012 13:46

“አታመልጭኝም” ነገ “ላፈቀርኩት” አርብ ይመረቃሉ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ያለን የበቀል ሂደት የሚተርከውና ችግር ችግርን ሲወልድ የሚያሳየው “አታመልጭኝም” ፊልም ነገ ሊመረቅ ነው፡፡ በሲኤልዲ ፕሮዳክሽን የተሰራውና ቀረፃው 2 ዓመት ተኩል የፈጀው ፊልም ነገ በሃገር ፍቅር በልዩ ፕሮግራም በምረቃ ከመታየቱ ባሻገር በ8፣10 እና 12 ሰዓት ላይ በሲኒማ አምፒር፣ በሲኒማ ኢትዮጵያ እና በአምባሳደር ሲኒማ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚታይ ታውቋል፡፡ “አታመልጭኝም” ፊልምን የደረሰውና ያዘጋጀው ሰይፉ ማሞ ሲሆን ከተዋናዮቹ መካከል ሰብለ ተፈራ፣ ሂሩት ኪሮስ፣ አበበ ባልቻና ዮሐንስ አፈወርቅ ይገኙበታል፡፡

በሌላም በኩል በደራሲና አዘጋጅ ጥላሁን ኃይሉ የተሰራውና ግዮን ፊልም ፕሮዳክሽን ያዘጋጀው “ላፈቀርኩት” ፊልም በመጪው አርብ በሲኒማ አምባሳደር፣ በሲኒማ አምፒር፣ በሴባስቶፓል ሲኒማ በኤድናሞል ማቲ ሲኒማ፣ ሰበታ በሚገኘው ጂም ሲኒማ፣ በአቃቂው ካፍደም ሲኒማ በአጐና ሠራዊት ሲኒማ፣ በደብረዘይት ሕይወት ሲኒማ እና በሌሎች ቦታዎች ይመረቃል፡፡ ኤርምያስ ሳህለማርያም፣ መሳይ ተፈራ፣ መሃመድ ሁሴን፣ ሳምራዊት ኤልያስና ሌሎችም ተውነውበታል፡፡ የ106 ደቂቃ ፊልሙን ለመሥራት አንድ ዓመት ያህል ፈጅቷል፡፡

 

 

Read 3162 times Last modified on Saturday, 25 February 2012 13:52