Saturday, 23 April 2016 10:11

እነ አቶ በቀለ ገርባ የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(14 votes)

   የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ተ/ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 22 ግለሰቦች ላይ አቃቤ ህግ የሽብር ክስ መስርቷል። በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት አቶ በቀለን ጨምሮ በአቶ ጉርሜሳ አያኖ የክስ መዝገብ የተካተቱት 22 ግለሰቦች፤ በሽብርተኝነት ከተፈረጀው የኦነግ አመራር ጋር በመገናኘት በኦሮሚያ ከተሞች አመፅና ብጥብጥ በማነሳሳት፣ የሰው ህይወት እንዲጠፋና ንብረት እንዲወድም አድርገዋል ይላል የአቃቤ ህግ ክስ፡፡
ትናንት የዋለው ችሎቱ ከተከሳሾች መካከል አማርኛ ቋንቋ መስማት የማይችሉ በመኖራቸው አስተርጓሚ ቀርቦ ክሳቸውን ለማብራራት መዝገቡን ለማክሰኞ ሚያዚያ 18 የቀጠረ ሲሆን ተከሳሾቹ የመብት ጥያቄ ካላቸው በቀጠሮው እለት ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልፆላቸዋል፡፡

Read 3930 times