Saturday, 25 February 2012 13:44

“አፀደ ወይን” ነገ፣ “ስውር ሰይፍ” እና “ተምሳሌቶቹ” ዛሬ ይመረቃሉ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(1 Vote)

በዲያቆን አሸናፊ ጌታነህ (ዘልደት) የተዘጋጁ ግጥሞች የተካተቱበት “አፀደ ወይን” “መጽሐፍ ነገ ይመረቃል፡፡ ገበያ ላይ ከዋለ አንድ ወር የሆነው መጽሐፍ ሐይማኖታዊ እና ማህበራዊ ጭብጦች የያዘ ነው፡፡ ከጧቱ 4፡30 በቅድስት ልደታ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚመረቀው መጽሐፍ ደራሲ የመጀመሪያ ሥራው ሲሆን ዲያቆን አሸናፊ የቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ የቲዎሎጂ ዲግሪ ተማሪ ነው፡፡ በሌላም በኩል በቅርቡ ለንባብ የበቃው የዮዲት ፈለቀ “ስውር ሰይፍ” የግጥም መድበል ዛሬ ከጧቱ 2፡30 በሀገር ፍቅር ትያትር ቤት ትንሿ አዳራሽ ይመረቃል፡፡ አቶ አያልነህ ሙላት፣ የደራሲያን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው በለጠ እና አንጋፋው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም በክብር እንግድነት ይገኛሉ ተብሎ በሚጠበቅበት የመጽሐፍ ምርቃት ፕሮፌሰር አቦነህ አሻግሬ እና ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል ሙያዊ አስተያየት ይሰጣሉ፡፡

የቪዲዮ ካሜራ ባለሙያ የሆነችው ዮዲት ፈለቀ “ስውር ሰይፍ” የመጀመሪያ የታተመ ሥራዬ ነው፡፡” ብላለች፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ በአዲስ አሰፋ የተዘጋጀው “ተምሳሌቶቹ የታሪክን አቅጣጫ ያስቀየሩና አለምን የቀደሙ እውነተኛ ጀግኖች “መጽሐፍ ዛሬ ከቀኑ 9፡30 ቦሌ በሚገኘው ቲኬ ሕንፃ ስምንተኛ ፎቅ አዳራሽ ይመረቃል፡፡ የአስር ታዋቂ ሰዎችን ታሪክ የያዘ ሲሆን በአዘጋጁ ያለ ነውጥ ለውጥ ያመጡ ተብለው ታሪካቸው ከተጠቀሱት መሃል ማህተመ ጋንዲ፣ ኔልሰን ማንዴላ፣ እማሆይ ቴሬሳ እና አብርሃም ሊንከን አሉባቸው፡፡ 206 ገፆች ያሉት መጽሐፍ በፎቶ ግራፎችም ታግዟል፤ ሲሆን ዋጋውም 38 ብር እና 12 ዶላር ሲሆን ያሳተመው ዩዝ ኢምፓክት ደቨሎፕመንት አሶሴሽን ነው፡፡

 

 

Read 1951 times Last modified on Saturday, 25 February 2012 13:46