Saturday, 16 April 2016 11:16

የአትሌቶች ስልጠና፣ አመጋገብና ጤና

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

• እንደ አትሌቶች ብዛት በቂ የአትሌቲክስአሰልጣኞችና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች የሉንም፤ ቢኖሩም
አሰራሩ አልተለመደም፡፡
• አትሌቶች በበቂ አሰልጣኞችና ድጋፍሰጭ ባለሙያዎቹ የሚሰሩ ከሆነ ለዶፒንግ ችግር
የሚጋለጡበት ሁኔታ ይቀንሳል፡፡
• ካልሽዬም፣ ዚንክ፣ አይረን በስነምግብባለሙያ በተፈጥሯዊ አግባብ መውሰድ ይቻላል፤ ዋናው
እውቀትን ማሳደግ ነው፡፡
• ንፁህ ስፖርተኛ ማለት 100% ጠንካራ ስራ፣ችሎታ እና ቁርጠኝነትን ከሳይንሳዊ ልምምድ ጋር አዋህዶ
የሚሰራ ነው፡፡
ዘሩ በቀለ ቶላ (ደረጃ 1 የአትሌቲክስ አሰልጣኞች ሌክቸረር

       የአትሌቲክስ ተመራማሪው አቶ ዘሩ በቀለ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በስፖርት ሳይንስ የተቀበ ሲሆን የማስተሬት ዲግሪያቸውን ደግሞ በአትሌቲክስ ስልጠና ሰርተዋል፡፡
በአይ.ኤ.ኤ.ኤፍ (IAAF) የአሰልጣኞች አሰልጣኝነት ደረጃ1 (LEVEL 1 ) ማዕረግ አላቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ
የአትሌቲክስ ፊዚዮሎጂ ከአልቲቲዩድ በሚያገናኝ ጥናት ፒኤችዲ ድግሪያቸውን በዩኒቨርስቲ ኦፍ ኩዋዙሉ ናታን ደቡብ አፍሪካ እየተከታተሉ ናቸው፡፡ አቶ ዘሩ በተማሪነት ዘመናቸው በአምቦ ዩኒቨርስቲ እግር ኳስ ቡድን ተጨዋች ነበሩ፡፡ ከዚያም አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቡድን አሰልጣኝ በመሆንም አገልግለዋል፡፡ የዩኒቨርስቲው ቡድን በእግር ኳስ ፌደሬሽን ተመዝግቦ የሚወዳደር ነበር፡፡ በ ስፖርት አ ስተዳደር ላይም አቶ ዘሩ በቀለ ሰፊ ልምድ
አላቸው፡፡ በ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወይንም በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የስፖርት ማህበር መስራችነት፤ ምክትል
ፕሬዝዳንትነት እና ዋና ፀሃፊነት ለስድስት አመታት አገልግለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ‹‹የኤክስትራ ካሪኩለር ኤንድ ስፖርትስ አሶሴዬትስ›› ዲን በመሆን ከመስራታቸውም በላይ በኢትዮጰያ ወርልድ ቴካንዶ ፌደሬሽንም በስራ አስኪያጅነት አገልግለዋል፡፡
ከአትሌቲክስ ጋር በተገናኘ ለተወሰኑ ግዜያት የፌደሬሽኑ ቴክኒክ ኮሚቴ ሆነው ከማገልገላቸውም በላይ አሁንም በከፍተኛ ደረጃ ባለሙያነት በተለያዩ ምርምሮች፤ የቡድን ጥናቶች ተሳትፎ በማድረግ እየተንቀሳቀሱ ናቸው፡፡
አቶ ዘሩ በቀለ በፀረ ዶፒንግ እንቅስቃሴ ከበለፀጉ አገራት ይልቅ በከፍተኛ ደረጃ መሰራት ያለባቸው ታዳጊ አገራት እንደሆኑ ያስገነዝባሉ፡፡ በንፁህና ሳይንሳዊ መንገድ በመስራት በአትሌቱ የተጋረጠውን የዶፒንግ አደጋ መከላከል
እንደሚቻል በማስረዳትም፤ በንፁህ ስፖርት የታዳጊ አገራት አትሌቶች በይበልጥ ተጠቃሚ መሆናቸውን በሚያስገነዝብ ሁኔታ ከስፖርት አድማስ ጋር ሰፊ ቃለምልልስ አድርገዋል፡፡
   የመጀመርያው ክፍል ከዚህ በታች የቀረበው ነው፡፡
በኢትዮጵያ ስፖርት እንደ ባለድርሻ አካል ብንመለከትዎ ብዙ ማጋነን አይደለም፡፡ ከትምህርትዎ በተገናኘ፤ በአስተዳደር
እና በስልጠና ካልዎት ልምድ አኳያ ምን ሲሰሩ ቆይተዋል፤ አሁንስ ምን እየሰሩ ነው….
በአትሌቲክስ ፌደሬሽኑ የቴክኒክ ኮሚቴ ባገለገልኩባቸው ዓመታት በተለይ ለታዳጊ እና የወጣት ፕሮጀክቶች ወጣት
አሰልጣኞች በርካታ ስልጠናዎችን ሰጥቻለሁ፡፡ በአካል ብቃት አሰልጣኝነት የሁለተኛ ደረጃ ፈቃድ በመያዜ ከአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሸን፤ ከጅምናስቲክ ፌደሬሽን እና ከወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ጋር በመሆን በአካል ብቃት አሰልጣኞች አሰልጣኝነት ብዙ ስልጠናዎችን ሰጥቻለሁ፡፡ በተረፈ አሁን በቅርቡ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ወቅታዊ ሁኔታን በሚዳስስ ልዩ ጥናት ላይ በሚሰራው ቡድንም እየሰራሁ ነው፡፡ ጥናቱ በፌደሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ በተሰየመ ቡድን እየተሰራ የሚገኝ ነው፡፡ ፌደሬሽኑ ወደፊት በይበልጥ የሚያብራራው ነው፡፡ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ወቅታዊ ሁኔታና አጠቃላይ እንቅስቃሴ ላይ ያተኩራል፡፡ ከታዳጊ እስከ ብሄራዊ ቡድን ያለውን እንቅስቃሴ የሚዳስስ ነው የሚሆነው፡፡
በርካታ የአትሌቲክስ አሰልጣኞችን አሰልጥነዋል፤ ከዚሁ ልምድ በመነሳት በአጠቃላይ የአትሌቶች ስልጠና በኢትዮጵያ
ያለበትን ወቅታዊ ደረጃ እና ሂደት እንዴት ይታዘቡታል፤ ያሉትንም ጉደለቶች ቢያነሱልን
… በክፍተት አኳያ ከተመለከትነው በአትሌቲክሱ በቂ አሰልጣኞች የሉም፤ ከመቶ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ባለባት አገር የአትሌቲክስ ባለሙያዎች ብዛት በቂ አይደለም፡፡ በአይ.ኤ.ኤ.ኤፍ ወይም በተለያዩ የአትሌቲክስ ተቋማት ደረጃ በከፍተኛ ደረጃ የተማሩ እና የሰለጠኑ አሰልጣኞች እና ባለሙያዎች የሉም፡፡ በጣም አነስተኛ ቁጥር ነው ያላቸው፡፡
ይህ ሁኔታ በየክለቡ እንዲሁም በየፕሮጀክቶች ተመልምለው እና ተቀጥረው ለሚሰሩ ስፖርተኞች ብዙ እክሎችን እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ሰልጣኝ አትሌቶች ከሚያሰለጥኗቸው ባለሙያዎች ብቃት እና ብዛት አኳያ በትክክል አስፈላጊ የሆነውን የአትሌቲክስ የስልጠና ፖሊሲ እ ና እ ድገት ደ ረጃ በ ማግኘት እ የሰሩ አ ይደሉም፡፡ ከብቃት አኳያ
እንደማንኛውም ስ ፖርት አ ትሌቲክሱም በውጤት ይለካል፡፡ በጥሩነሽ ዲባባ እና በወጣቶች ስፖርት አካዳሚ የሚገኙ ሰልጣኞች በተለያዩ ክለቦች እና ብሄራዊ ቡድንም አሰልጣኞች እና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች በተወሰነ መልኩ እየገቡ መሆናቸው ተስፋ ይሰጣል፡፡ በአጠቃላይ ግን ከመሰረተ ልማት፤ ከሙያዊ መሳርያዎች፤ ከስፖርት ቁሳቁሶች፤
ከሳይንሳዊ አሰራር ምዝገባ እና ስሌት አንፃር በአገር አቀፍ ደረጃ ያለውን አቅም ስንመለከት በትክክል አስተማማኝ
ነው ብሎ ለመናገር ይከብዳል፡፡ አሰልጣኞች በቂ ድጋፎችን እያገኙ አይደለም፤ በተለያዩ አቅም ግንባታዎችም የሚታገዙም ባለመሆናቸው የሙያ ደረጃቸውን እያሻሻሉ አይደለም፡፡ የማሰልጠኛ መሰረተ ልማቶች፤ ከጅምናዚዬም ፤ ከትራኮች፤ ከተፈጥሯዊ መሮጫ ስፍራዎች ሳሮች እና አቀበት ቁልቁለት መስርያ ጫካዎች በአጠቃላይ ከውጫዊ ተፅእኖዎች አንፃር ያሉ ተግዳሮቶች ላይ አገር አቀፍ ጥናት መሰራት እንዳለበት ነው የማምነው፡፡ በአትሌቲክስ አሰልጣኞች ወቅታዊ የስራ ሂደት ያሉ ውስጣዊ እና ውጫዊ ምክንያቶችን ለይቶ ለማወቅጥናት ማስፈለጉን
አስገነዝባለሁ፡፡ በጠቅላላው ስንመለከተው ግን በአትሌቲክሱ ስፖርት የተወሰኑ አሰልጣኞች፤ በማዘወተሪያ
ስፈራ፤ በስልጠና መሳርያዎች፤ በጤና እና አመጋገብ ባለሙያዎች ተ ደግፈው የ ሚሰሩ ቢሆንም በ አመዛኙ ያለው
ሁኔታ ግን ብዙዎቹ አሰልጣኞች ሁሉ ነገር ተሟልቶላቸው በዘመናዊ ስልጠና ስርዓት በስፋት እየሰሩ አይደለም፡፡
ሳይንሳዊ የስልጠና መንገዶችን በአግባቡ ተጠቅመው የሚሰሩ በጣም ጥቂት አሰልጣኞች መሆናቸው ያሳስባል፡፡ ይህ ሁኔታም አሰልጣኞች እየሰሩበት ያለውን ብቃት በትክክል ለመገምገም አዳጋች ያደርገዋል፡፡ በመጀመርያ ደረጃ አንድ አሰልጣኝ 40 ስፖርተኞችን የሚያሰልጥን ሲሆን እንዴት አይነት ሳይንሳዊ ልኬት የስራ ሁ ኔታውን እንደሚገመግም
መረዳት ይ ከብዳል፡፡ አሰልጣኞችን ሳይንሳዊ ስልጠና እየተከተላችሁ አይደለም፤ የምትከተሉት ስልጠና በቂ የሳይንስ ሁኔታ የሚያገናዝብ አይደለም ብሎ በአሰልጣኞቹ ላይ ለመፍረድ አንችልም፡፡ የተወሰኑ ክለቦች ጅምናዚዬሞችን በመገንባት እና መሰረተ ልማቶቻቸውን በጥቂቱ አሟልተው መስራታቸው ለአሰልጣኞች የተደራጀ አሰራር አስተዋፅኦ አለው፡፡ ካምፕ ባለቸው ክለቦች ላይ የሚሰሩ አሰልጣኞች የልጆቻቸውን ብቃት ለማሳደግ በተበታተነ መንገድ ከሚሰሩት የተሻለ እድል አላቸው፡፡ ከዚያ ባለፈ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው
በሳይንሱ የሚማሩ አሰልጣኞች አሉ፡፡ ከእነሱ መካከል ጥቂቶቹ በጣም ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ አትሌቶችን ብቃት በማሳደግ ለውጥ እያመጡ የሚገኙ፤ ከፕሮጀክቶች ጀምረው እየሰሩ ስኬታማ ሂደትን ያሳዩ አሰልጣኞችም አሉ፡፡ በአብዛኛው ግን የተሟላ ነገር ባለመኖሩ በአገር አቀፍ ደረጃ በትክክል ሳይንሳዊስልጠና ተግባራዊ እየሆነ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡
እንግዲህ በአትሌቲክሱ የተደራጁ የስልጠና መዋቅሮች፤መሰረተ ልማቶች እና ባለሙያተኞች አለመኖራቸውንአረጋግጠዋል፡፡ ይሄው በአሰልጣኞች ስራ የተፈጠሩ ጉድለቶች
ስፖርቱን ምን እያሳጡት ናቸው፡፡ በቅርቡ የተከሰተውየዶፒንግ ችግርም በአጠቃላይ ከዚህ ሁኔታ ጋር የሚገናኝበትአቅጣጫም ያለ ይመስላልአሁን ከዶፒንግ ጋር በተገናኘ መመልከት ይቻላል፡
፡ ሳይንሳዊ ስልጠና በፀረ ዶፒንግ እንቅስቃሴ በግድ አስፈላጊነው፡፡ የሰልጣኞችን የዕለት ተዕለት የልምምድ፤ የአመጋገብ፤የጤና ስርዓት በማወቅ ብቃታቸውን በመገምገም በመስራት
ለውጥ መፍጠር ይቻላል፡፡ በሳይንሳዊ አካሄድ እያደጉ እናእየወረዱ የሚመጡ አትሌቶችን በአግባቡ መለየት ይቻላል፡፡አንድ አሰልጣኝ በዚህ መንገድ በቂ የሆነ አሰራር ካለው ውጤት
ማምጣቱ አይቀርም፡፡ የአትሌቶችን የዶፒንግ ተጋላጭነትምመከላከል የሚቻል ነው፡፡ የአሰልጣኝ እና የሰልጣኞቹ ብዛትየተመጣጠነ መሆኑ ይህን ሳይንሳዊ አካሄድ ውጤታማያደርገዋል፡ በአጠቃላይ ሳይንሳዊ አሰራር የሰልጣኝ አትሌቶችንበአግባቡ መከታተል፤ የወሰዷቸውን መድሃኒቶች የመቆጣጠር፤የሚሰሩትን ልምምድ የመተግበር፤ የመመዝገብ የመለካት እናየማስላት ተግባራትን ማከናወን ያስችላል፡፡ በርካታ አትሌቶችባልተመጣጠነ የአሰልጣኝ እና ባለሙያ ብዛት ይዞ መንቀሳቀስሳይንሳዊ አካሄድ አይደለም፡፡እዚህ ጋር አንድ በአጠቃላይ የምገልፀው ጉዳይ አለ፡
፡ በአገራችን በተደጋጋሚ እንደሚስተዋለው የስልጠና ስራበትርፍ ሰዓት የሚሰራ ሙያ እይደለም፤ የሙሉ ጊዜ ስራመሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ማንኛውም አሰልጣኝ የአንድንአትሌት ብቃት ለማሳደግ በሙሉ ግዜ 24 ሰዓታትን መስራትይጠበቅበታል፡፡ የልምምድ ሂደቱን በየጊዜው በመመዝገብ፤
የተወዳደረበትን ስፍራ ፤ ያስመዘገበውን ውጤት፤ የወሰደውንመድሃኒት፤ የበላውን ምግብ በአግባቡ ተከታትሎ እና በግልቅርበት ሊሰራ የሚችል ከሆነ ሳይንሳዊ አሰራር ለመከተልያግዛዋል፡፡ በአጠቃላይ አሰልጣኞች በዚህ መንገድ እንዳይሰሩከአስተሳሰብ ባሻገር ትልቁ ችግር የኢኮኖሚ ጉዳይና አቅምነው፡፡የአትሌቲክስ ስልጠናዎች በሳይንሳዊ መንገድአለመከናወናቸው ግን በርግጥም ብዙ ነገር እያሳጡን ናቸው፡፡በመጀመርያ ደረጃ አትሌቶቻችን ተበታትነው የሚገኙት፡፡ ግማሹ
በስልጠና ሂደቶች ካለመርካት የተነሳ ወደ አውሮፓ ይሄዳሉ፡፡ በማናጀሮች ምክር እና በሌሎች አማካሪዎች እገዛ ለመስራትይገዳዳሉ፡፡ የተለያዩ መድሃኒቶችና አበረታች ሰፕለመንቶች
ለመውሰድ እየተገደዱ ናቸው፡፡ እውነቱን ለመናገር በሳይንሳዊየስልጠና መንገዶች በበቂ ሁኔታ በአገር ውስጥ መስጠትከታቸለ ብዙ ችግር ውስጥ አንገባም፡፡ የአሰልጣኞች እናየሰልጣኞች ብዛትን ማመጣጠን የመጀመርያው ተግባር ይሆናል፡

Read 2690 times