Saturday, 25 February 2012 13:41

አላቲኖስ በ”ሼፉ” ላይ ይወያያል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

አላቲኖስ የፊልም ሰሪዎች ማህበር በቅርቡ ለተመልካች ቀርቦ አትኩሮት እየሳበ ያለውን “ሼፉ” ፊልም ለውይይት እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡ የመሃመድ ዳውድ ዝግጅት የሆነው “ሼፉ” ለውይይት የሚቀርበው በመጪው ሐሙስ ከቀኑ 11 ሰዓት ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የሩስያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል ፑሽኪን አዳራሽ ነው፡፡ በውይይቱ ከሌሎች ፊልም አፍቃሪዎች፣ ከአዘጋጁ እና ከማህበሩ አባላት ሌላ በፊልሙ የተለየ የትወና ብቃት አሳይታለች ተብላ የተወሰደችው የፊልሙ ተዋናይ ማህደር አሰፋ ትገኛለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Read 1201 times