Saturday, 25 February 2012 13:38

“ሁአዌ” ሞባይል ብሮድባንድ ትዕይንት ያቀርባል ኦል አፍሪካ የቆዳ አውደርእይ ዓርብ ይከፈታል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

 

በሽያጭ በዓለም ሁለተኛው ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያ የሆነው የቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ በመጪው አርብ በዋናው ፖስታ ቤት ግቢ ውስጥ የተንቀሳቃሽ ሞባይል ብሮድባንድ የጎዳና ላይ ትዕይንት ማክሰኞ ያቀርባሉ፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም፣ አይሲቲ ማህበረሰብ ተማሪዎችና ሌሎች በትዕይንቱ ይሳተፋሉ፡፡
ባለፈው ዓመት 26 ቢሊዮን ዶላር ያተረፈው ሁዋዌ በቴሌኮም መሠረተ ልማት ዝርጋታ በአገልግሎት መስጫ፣ የቴሌፎን ዲቫይስ በማቅረብ የሚታወቅ ሲሆን በተለይ በኔትዎርክ ሥራ ትልቅ ቢዝነስ አለው፡፡ ዋና መቀመጫው ሺንዞን ቻይና የሆነውና በ120ሺህ ሠራተኞች በ140 ሀገራት የሚንቀሳቀሰው “ሁዋዊ” ካሁን ቀደም በኢትዮጵያ በገጠር ኮኔክቲቪቲና የሦስተኛው ትውልድ ስልክ አቅርቦት ላይ የሠራ ሲሆን የአራተኛው ትውልድ ቴሌኮምን በኢትዮጵያ አልጀመረም፡፡ የሞባይል ኔትዎርክ ችግርን አስመልክቶ ደንበኞች እያማረሩ ባለበት ወቅት ስለብሮድባንድ ሞባይል ይታሰባል ወይ ያልናቸው ዝግጅቱን የሚያስተባብረው የታሚሶል ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ  ሰለሞን ከበረ “ኢትዮ ቴሌኮም ማስፋፊያ እየሰራ ነው፡፡ እየተሻሻለ ይሄዳል ያ ሲጠናቀቅ ከሚሰሩት አንዱ ሞባይል ብሮድባንድ ነው፡፡ የአሁኑን አይነት ትዕይንት ሁዋዌ በደቡብ አፍሪካ፣ ሊቢያ፣ ኬንያና ሌሎችም ሀገራት አሳይቷል፡፡” ብለዋል፡፡
በሌላም በኩል ኦል አፍሪካ የቆዳ አውደርዕይና ባዛር ከመጪው አርብ እስከ እሁድ በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ አዘጋጁ የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር ነው፡፡ የዝግጅቱ አስተባባሪ ሕኖፍ ፋሚሊ ትሬዲንግ ኃ.የተ የግል ማህበር ዋና አስተባባሪ አቶ ኤርምያስ ከበደ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፁት ታዋቂ ሞዴሎችና አርቲስቶች የቆዳ አልባሳት፣ ቦርሳዎች፣ ጌጣጌጥ፣ ጫማዎችና ሌሎች ምርቶች በዝግጅቱ ያስተዋውቃሉ፡፡ በዚህ ዝግጅት ከሚሳተፉት መካከል ዲዛይነር ሚና ተፈራ፣ ሞዴልና ተዋናይ እፀሕይወት አበበ እና አርቲስት መሃመድ ሚፍታ ይገኙበታል፡፡

 

በሽያጭ በዓለም ሁለተኛው ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያ የሆነው የቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ በመጪው አርብ በዋናው ፖስታ ቤት ግቢ ውስጥ የተንቀሳቃሽ ሞባይል ብሮድባንድ የጎዳና ላይ ትዕይንት ማክሰኞ ያቀርባሉ፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም፣ አይሲቲ ማህበረሰብ ተማሪዎችና ሌሎች በትዕይንቱ ይሳተፋሉ፡፡ ባለፈው ዓመት 26 ቢሊዮን ዶላር ያተረፈው ሁዋዌ በቴሌኮም መሠረተ ልማት ዝርጋታ በአገልግሎት መስጫ፣ የቴሌፎን ዲቫይስ በማቅረብ የሚታወቅ ሲሆን በተለይ በኔትዎርክ ሥራ ትልቅ ቢዝነስ አለው፡፡ ዋና መቀመጫው ሺንዞን ቻይና የሆነውና በ120ሺህ ሠራተኞች በ140 ሀገራት የሚንቀሳቀሰው “ሁዋዊ” ካሁን ቀደም በኢትዮጵያ በገጠር ኮኔክቲቪቲና የሦስተኛው ትውልድ ስልክ አቅርቦት ላይ የሠራ ሲሆን የአራተኛው ትውልድ ቴሌኮምን በኢትዮጵያ አልጀመረም፡፡ የሞባይል ኔትዎርክ ችግርን አስመልክቶ ደንበኞች እያማረሩ ባለበት ወቅት ስለብሮድባንድ ሞባይል ይታሰባል ወይ ያልናቸው ዝግጅቱን የሚያስተባብረው የታሚሶል ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ  ሰለሞን ከበረ “ኢትዮ ቴሌኮም ማስፋፊያ እየሰራ ነው፡፡ እየተሻሻለ ይሄዳል ያ ሲጠናቀቅ ከሚሰሩት አንዱ ሞባይል ብሮድባንድ ነው፡፡ የአሁኑን አይነት ትዕይንት ሁዋዌ በደቡብ አፍሪካ፣ ሊቢያ፣ ኬንያና ሌሎችም ሀገራት አሳይቷል፡፡” ብለዋል፡፡

በሌላም በኩል ኦል አፍሪካ የቆዳ አውደርዕይና ባዛር ከመጪው አርብ እስከ እሁድ በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ አዘጋጁ የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር ነው፡፡ የዝግጅቱ አስተባባሪ ሕኖፍ ፋሚሊ ትሬዲንግ ኃ.የተ የግል ማህበር ዋና አስተባባሪ አቶ ኤርምያስ ከበደ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፁት ታዋቂ ሞዴሎችና አርቲስቶች የቆዳ አልባሳት፣ ቦርሳዎች፣ ጌጣጌጥ፣ ጫማዎችና ሌሎች ምርቶች በዝግጅቱ ያስተዋውቃሉ፡፡ በዚህ ዝግጅት ከሚሳተፉት መካከል ዲዛይነር ሚና ተፈራ፣ ሞዴልና ተዋናይ እፀሕይወት አበበ እና አርቲስት መሃመድ ሚፍታ ይገኙበታል፡፡

 

 

Read 2172 times