Saturday, 16 April 2016 10:45

የኢኮኖሚ እድገቱ ወደ 4.5 በመቶ ያሽቆለቁላል - IMF

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(9 votes)

መንግስት በ7 በመቶ ያድጋል ብሏል
     እንደወትሮው መንግስት እና የዓለም ገንዘብ ድርጅት፣ የኢኮኖሚ እድገትንበተመለከት ያወጡት  መረጃ ዘንድሮም የተራራቀ ሆኗል፡፡ ባለፉት አስር ዓመታት ኢኮኖሚው በአስር በመቶ ሲያድግ መቆየቱን መንግስት የሚገልፅ ሲሆን፣ የዓለም ገንዘብ ድርጅት በበኩሉ፤ የእድገቱ መጠን 8 በመቶ ገደማ እንደነበረ ይናገራል፡ ፡ ዘንድሮ በድርቁ ሳቢያ ኢኮኖሚው እንደሚቀዛቀዝ አከራካሪ  ባይሆንም፤ ሁለቱም ያቀረቡት መረጃ ይለያያል፡፡ አይኤምኤፍ ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት፤   ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንደእስካሁኑ በ8 በመቶ እንደሚያድግ ተገምቶ እንደነበር አስታውሶ፣ በድርቅ ሳቢያ የኢኮኖሚ እድገቱ ወደ 4.5 በመቶ ዝቅ ይላል ብሏል፡፡ በሚቀጥለው ዓመት ግን፣ እንደቀድሞው ፈጣን እድገት ሊመዘገብ ይችላል ብሏል - አይ ኤም ኤፍ፡፡ በዚህ ዓመት ስራ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችም እየቀናቸው አለመሆኑንም ሪፖርቱ አትቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ፤ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ፈጣን እድገት እያስመዘገበ
እንደሚቀጥል ጠቅሰው፤ ዘንድሮ ድርቁ ተፅእኖ ቢኖረውም የኢኮኖሚ እድገት ከ7 በመቶ ያነሰ አይሆንም ብለዋል፡፡ ከአፍሪካ ሀገራት አይቮሪኮስት፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ሴኔጋል እና ታንዛኒያ እስከ 7 በመቶ እድገት በማስመዝገብ የሰመረ አመት ይሆንላቸዋል ብሏል አይኤምኤፍ፡

Read 4766 times