Saturday, 13 February 2016 11:32

“የሱፍ አበባ” መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  በማሕሌት ኪዳነወልድና በናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በደራሲ አለባቸው ሀብታሙ የተፃፈውና  በብርሃነመስቀል ረዳ የፖለቲካ ሰብዕናና ህይወት ላይ የሚያጠነጥነው “የሱፍ አበባ” የተሰኘው መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡
መጽሐፉ የኢህአፓ ከፍተኛ አመራሮችን በተለይም የብርሃነ መስቀል ረዳን ፖለቲካዊ ሥነ-ልቦና፣ ፖለቲካዊ ቁመናና ፖለቲካዊ እሳቤ በጥልቀት ይተነትናል የተባለ ሲሆን በተጨማሪም ብርሃነ መስቀል ረዳ ከነጌታቸው ማሩ፣ ዘሩ ክሽሸን፣ ክፍሉ ታደሰና ዶክተር ተስፋዬ ደበሳይ ጋር በከተማ ትጥቅ ትግል ዙሪያ ዙሪያ የነበረውን የከረረ ቅራኔም ቁልጭ አድርጐ እንደሚያሳይ ተገልጿል፡፡ 379 ገፆች ያሉት መጽሐፉ፤ በ91 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ሊትማን ቡክስ እያከፋፈለው ይገኛል፡፡ ደራሲው ሀብታሙ አለባቸው፤ ከዚህ ቀደም “አውሮራ” እና “የቄሳር እንባ” የተሰኙ ፖለቲካዊ ልቦለዶችን ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል፡፡

Read 4583 times