Saturday, 06 February 2016 11:38

ኤሎሄ !

Written by  (በትዕግስት ገሠሠ)
Rate this item
(10 votes)

ጊዜ ሆይ፤
ከዘመን ኃፍረትሽ ሽሽት፣ ከል ኩታውን
ተከናንበሽ
የጠይቡን ሰው እድሜ ጥለት፤
በደሙ ላብእምባ ማሾ፣ በሚያጥበረብረው
እልፍኝሽ
ግዞት አውጆ እፎይ በሚል፣ የፍርደ ገምድልሽ
ሰገነት፤
አንድ እኔው ብቻ ማለትሽ
ተማምነሽ...
እጅ አልነሳ ያለሽን ሁሉ፣ በሚኮደኩድልሽ
ሰንሰለት!
እንደ እውነትማ ንትበት፣ እንደ በደለኛው
ንቅዘት
ቢበዛልሽ እንጂ ካቴና
ሀቅማ ገና...!!!
2
ጊዜ ሆይ፤
እንዲህ እንደዛሬው፣ ሰው አቅሉ ሳይያዝ
በአማን ሳለ ገና፤
የቤቱ በረከት በአለም ገንኖ ነበር ገድሉ
የሚሰማ፡፡
እግሮቹን ከጉርጓድ ከእምጥ ስምጥ አውጥቶ
አድማስ እየናደ
አለቱን ፈልፍሎ በጥበብ ያነፀ የባለጅን ትጋት
ወርሶ ባዋደደ፤
በማይብለጨለጭ የወጥ ድንጋይ ውበት፣
ምድሪቱን ያስራደ
ፍጥረት ዋሻ ሳለ ከፍ ብሎ የሚታይ ነበረ
ከተማ ገዝፎ የከበደ፤
የሰማይ ጠቀስ ክብሩን፣ምንጩን ያልዘነጋ፣ከሳር
ቅጠሉ ኑሮው የተዋሀደ
ያ እፁብ ድንቅ ማንነት፣ ልዕለ ሰብዕና፣ ከወገኔ
መሀል አሁን ወዴት ሄደ ?
3
ጊዜ ሆይ፤
የቀዬአችን ማገር፣ ምሰሶና ወጋግራ፣ የእርካቡ
አባወራ፣ ባለ ጊዜሽ ሁላ
ኩሩ ተጠዋሪው በቡድን ቱማታ የባቢሎን
 ዘመን  ግምብ  እየቀለሰ፤
እንሆ የኛ ትውልድ በግርምቢጥ ሸንጎ የእንካ
ሰላንቲያ ክስ
ከሽቦ አጥሩ እግር ብረት፣ ሳጉ እማይሰማን
አህህ ባለቀሰ፤
ከዜጋው እጣ ፈንታ የእለት ተለት አሳር
ተገንጥሎ ቆሞ
ተሰይሜአለሁ  የሚል፣ የፍትህ ርትዕ ካፊያው
ያላረሰረሰ፤
ችሎት ያንጎላጃል ‹‹ህዝቡን አትቀስቅሱ!››
ብሎ እየከሰሰ
ሀገር ክንፍ አውጥቶ በአየር በደም መና
 እየተላወሰ!!!
ኦ !  ጊዜ ሆይ . . . ! ? !

Read 4430 times