Print this page
Saturday, 18 February 2012 10:51

የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዳይሬክተሪ ነገ ይመረቃል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በዘርፉ የመጀመርያ የሆነና የኢትዮጵያን የቱሪዝም ቅርሶች የሚያስተዋውቀው ዳይሬክተሪ ነገ ከቀኑ 11 ሰዓት መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተክርስትያን ፊት ለፊት በሚገኘው ወይን ኢትዮጵያ የባህል ምግብ አዳራሽ ይመረቃል፡፡ደረጃውን በጠበቀ ወረቀት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን Ethiopian Tourism Directory ቅፅ 1 ሙሉ ቀለም ከ200 ገፆች በላይ ያለውን ቱሪዝም ማውጫ ያዘጋጀው ቪዚት ቱ ኢትዮጵያ መቀመጫውን ቤልጅየምና ኢትዮጵያ ያደረገ የቱሪዝም ድርጅት ነው፡፡

በ10 ሺህ ቅጂ ለመጀመርያ ጊዜ የታተመው የቱሪዝም ማውጫ መፅሐፍ የሀገሪቱን ዋነኛ የቱሪስት መስህቦች፣ የአስጐብኚና የጉዞ ወኪሎች፣ ማህበረሰባዊ ቱሪዝም፣ የአንድ ቀን ቤተመዘክር ጉብኝት በአዲስ አበባ የሚሉና ሌሎች ርእሶች የያዘ ነው፡፡ የዳይሬክተሪው ዳይሬክተር እና ዋና አዘጋጅ አቶ ቴዎድሮስ መርአዊ ስጦት ለመጀመርያ ጊዜ መዘጋጀቱን አስመልክቶ “በአይነቱ የመጀመርያው ቢሆንም በውስጡ ያለው መረጃ የተሟላ ባይሆንም በጣም ይጠቅማል” ብሏል፡፡

 

 

 

Read 1016 times Last modified on Saturday, 18 February 2012 10:54