Print this page
Saturday, 18 February 2012 10:49

“ዴርቶጋዳ” የእንግሊዝኛ እትም ዛሬ ይመረቃል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

“ዴርቶጋዳ” በይስማዕከ ወርቁ ተደርሶ በከፍተኛ ደረጃ የተነበበ መፅሐፍ በእንግሊዝኛ በተመሳሳይ ርዕስ ተተርጉሞ ባለፈው ሳምንት ለንባብ የበቃ ሲሆን ዛሬ በሚካሄድ የጥበብ ድግስ እንደሚመረቅ ዩኒቲ አሳታሚ አስታወቀ፡፡ ከቀኑ 10፡30 የሚካሄደው ምርቃት የሚከናወነው በሩስያ የሳይንስ እና ባህል ማዕከል ፑሽኪን አዳራሽ ነው፡፡ በ74 ብር ከ99 ሳንቲም እና በ12.99 የአሜሪካ ዶላር ለገበያ የቀረበው ባለ 358 ገፅ ልቦለድ መፅሐፍን ወደ እንግሊዝኛ የተረጐሙት አቶ ዘላለም ንጉሴ ሲሆኑ የታተመውም በፋር ኢስት ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ነው፡፡

Read 1553 times