Saturday, 18 February 2012 10:46

የጋዜጠኛ ፅጌረዳ ኃይሉ መታሰቢያ ጋዜጠኞች ውድድር ተጠናቀቀ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በቅርቡ ከወሊድ በኋላ ህይወቷ ያለፈውን ጋዜጠኛና ደራሲ ፅጌረዳ ኃይሉን የሚዘክር የሥነ ፅሁፍ ውድድር ተካሂዶ ከትናንት ወዲያ ተጠናቀቀ፡፡ “ሁሉም” በተባለና በህፃናት አድን ድርድት በሚታገዝ ድርጅት የተዘጋጀው ውድድር በህትመት፣ በኤሌክትሮኒክስ እና ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ዘርፎች የተካሄደ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ታከለ ወርቁ በህትመት፣ ይድነቃቸው ለማ በኤሌክትሮኒክስ እና ሜሮን ተክለብርሃን በማህበራዊ ዘርፎች ውድድር በማሸነፍ ተሸልመዋል፡፡ በየዘርፎቹ ሁለተኛ እና ሦስተኛ የወጡትም ከትናንት ወዲያ በሐርመኒ ሆቴል በተከናወነ ሥነ ሥርዓት መሸለማቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡ ተሸላሚዎቹ ከቶሽባ ላፕቶች እስከ ሶኒ 14 ሜጋ  ፒክልስ ካሚራና ኤክስተርናል ሃርድ ዲስክ ተሸልመዋል፡፡ ጋዜጠኛ ፅጌረዳ ኃየሉ በውድድሩ ለመሳተፍ ተመዝግባ ስለነበር እና “ሁሉም” እናቶች ጤና ዙርያ ስለሚሰራ ውድድሩ በሷ ስም መዘጋጀቱን ማወቅ ተችሏል፡፡

Read 1163 times Last modified on Saturday, 18 February 2012 10:47