“ዘ ግሬተስት ሂትስ” የተባለው አልበም በቢልቦርድ ምርጥ 200 አልበሞች በ64ሺ ኮፒ ሽያጭ 6ኛ ደረጃ መያዙን የኔልሰን ሳውንድ ስኪን ሪፖርት አመልክቷል፡፡ በ1986 የሰራችው “ዊትኒ ሂውስተን” የተባለው አልበሟ፤ “ቦዲጋርድ” የተሰኘው ፊልም ማጀቢያ ሙዚቃና የመጨረሻ ስራዋ “አይሉክ ቱ ዩ” ገበያቸው እንደደራ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የአልበሞቿ አሰራጭ ሶኒ፣ በአልበሞቹ ዋጋ ላይ እጥፍ ጭማሪ አድርጎ ለጥቂት ቀናት ሲቸበችብ ከቆየ በኋላ ከፍተኛ ትችት ተሰንዝሮበት ይቅርታ በመጠየቅ የአልበሞቹ ዋጋ ወደ ቀድሞው ሊመለስ ችሏል፡፡