Saturday, 23 January 2016 13:20

የትራንስፎርመር መፈንዳት የኤሌክትሪክ መቆራረጥ አስከትሏል ተባለ

Written by  መንግሥቱ አበበ
Rate this item
(3 votes)

ሰሞኑን በአዲስ አበባ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ትራንስፎርመር በመፈንዳቱና በኃይል ጭነት መጨናነቅ የተፈጠረ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
በተለይ በመካኒሳ አካባቢ 39 ሜጋ ዋት ትራንስፎርመር በመቃጠሉ የአካባቢው ነዋሪ ለሁለት ቀናት ኤሌክትሪክ አለማግኘቱን የጠቀሱት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ገ/እግዚአብሔር አዲሱ፤ የኃይል ጥራት ባይኖረውም የመብራት መቆራረጥ ያጋጠማቸው አካባቢዎች በኃይል ውሰት ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል፡፡
በሌሎች የከተማዋ አካባቢዎች በተለይ የኃይል ጭነት ለኤሌክትሪክ መቆራረጡ መንስኤ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው፤ የመስመሮቹን መጨናነቅ ለመቀነስ ሲባል የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚቋረጥ ተናግረዋል፡፡ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የማሰራጫ መስመሮችን አቅም ማሻሻል ስለሚያስፈልግ ከውጭ ኩባንያ ጋር የ6 ሚ. ዶላር ስምምነት መፈረሙን የተናገሩት አቶ ገ/እግዚአብሔር ተግባራዊ ስራውም በመጪው የካቲት ወር ይጀምራል ብለዋል፡፡

Read 1514 times