Print this page
Saturday, 18 February 2012 10:31

ቫለንታይን የፊልሞችን ገበያ አነቃቅቷል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

በሶኒ የተሰራው “ዘ ቮው” የተሰኘ ሮማንቲክ ድራማ ፊልም በቦክስ ኦፊስ ሳምንታዊ የገቢ ደረጃ እየመራ ይገኛል፡፡ ባለፈው ሳምንት በሰሜን አሜሪካ ታይቶ 41.2 ሚሊዮን ዶላር አስገብቷል፡፡በማይክል ስቱሲ ዲያሬክት የተደረገው ፊልሙ 30 ሚሊዮን ዶላር እንደፈጀ ታውቋል፡፡ ከሰሜን አሜሪካ ውጭ በ20 የገበያ መዳረሻዎች ለዕይታ ቀርቦ 9.7 ሚሊዮን ዶላር ያስገኘው ይሄው ፊልም፤ በአጠቃላይ ከመላው ዓለም 52.4 ሚሊዮን ዶላር እንዳስገባ ተመዝግቦለታል፡፡የዴንዝል ዋሽንግተን “ሴፍ ሃውስ” የተሰኘ ፊልም 40.2 ሚሊዮን ዶላር በማስገባት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ በቫለንታይን ሰሞን ከታዩ አዳዲስ ፊልሞች ቢያንስ አራቱ በሰሜን አሜሪካ ብቻ ከ20 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንዳስገቡ የጠቆሙ መረጃዎች፤ ቫለንታይን የፊልሞችን ገቢ እንዳነቃቃው ይጠቁማል፡፡

 

 

Read 1169 times Last modified on Saturday, 18 February 2012 10:35