Saturday, 02 January 2016 12:15

ለ33 የከንፈርና ላንቃ ስንጥቅ ህሙማን ነፃ ህክምና ተሰጠ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(6 votes)

    በተፈጥሮ የከንፈርና ላንቃ ስንጥቅ ችግር አጋጥሟቸው ለዓመታት በከፍተኛ የጤና ችግር ሲሰቃዩ ለቆዩ 33 ህፃናትና ወጣት ህሙማን በሶማሌ ክልል ጐዴ ሆስፒታል ነፃ የቀዶ ህክምና አገልግሎት ተሰጣቸው፡፡
በፕሮጀክት ሐረር ኢትዮጵያ አስተባባሪነት፣ በጐዴ ሆስፒታል በተከናወነው የነፃ ህክምና ፕሮግራም ላይ ለህሙማኑ የቀዶ ህክምናውን ያደረጉት የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ይድነቃቸው ወ/መስቀል ናቸው፡፡
የፕሮጀክት ሐረር ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ወ/ሮ አይናለም ተፈራ እንደተናገሩት፤ በሶማሌ ክልል በጐዴ ሆስፒታል ውስጥ የተከናወነውን የከንፈርና ላንቃ ስንጥቅ ህሙማን ህክምና ለማግኘት 38 ሰዎች ተመዝግበው 33ቱ ህክምናውን ለማግኘት ብቁ ሆነው በመገኘታቸው ነፃ ህክምናው ተሰጥቷዋል፡፡
ህሙማኑ ከቀዶ ህክምናውንና መድሃኒቱንም በነፃ ማግኘታቸውን ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል፡፡
ፕሮጀክት ሐረር ኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎችን በማስተባበር በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የከንፈርና ላንቃ ስንጥቅ ህሙማን፣ ነፃ የቀዶ ህክምና እንዲያገኙ በመንቀሳቀስ ላይ ሲሆን በአመት አንድ ጊዜም ከተለያዩ የዓለም አገራት ብቁ ባለሙያዎችን ወደ አገር በማምጣት ከፍለው መታከም የማይችሉና በተለያዩ ከባድ የጤና ችግሮች የተያዙ ህሙማን ነፃ የምርመራ፣ የህክምና፣ የመድሃኒት አቅርቦትና የማገገም አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያደርግ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡  

Read 3303 times