Print this page
Saturday, 12 December 2015 11:58

የካጋሜን ስልጣን የሚያራዝመው ማሻሻያ ህዝበ ውሳኔ ይደረግበታል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 - ማሻሻያው ድጋፍ ካገኘ፣ ካጋሜ ለመጪዎቹ 19 አመታት በስልጣን ላይ ሊቆዩ ይችላሉ
    የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በ2017 በሚካሄደው የአገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ እንዲሳተፉ ለማስቻል ታስቦ በህገ መንግስቱ ላይ የተደረገውን ረቂቅ ማሻሻያ በተመለከተ በመጪው ሳምንት ህዝበ ውሳኔ እንደሚደረግ ቢቢሲ ዘገበ፡፡
በህገ መንግስቱ ላይ ሊደረግ የታሰበው ማሻሻያ በህዝበ ውሳኔው አብላጫ ድጋፍ ካገኘ፣ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ እስከ 2034 ድረስ በስልጣን ላይ መቆየት የሚችሉበት ዕድል ይፈጠርላቸዋል ያለው ዘገባው፣ የአገሪቱ ሴኔትም ፕሬዚዳንቱን በስልጣን ላይ ለማቆየት ታስቦ የተዘጋጀውን የህገ መንግስት ማሻሻያ ባለፈው ወር እንደተቀበለው አስታውሷል፡፡
አሜሪካ በ2017 የስልጣን ዘመናቸው ለሚያበቃው ለሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ፣ #እባክዎት በሰላም ስልጣንዎን ይልቀቁና ለአካባቢው አገራት መንግስታት አርአያ ይሁኑ” ስትል ጥሪዋን ብታስተላልፍም፣ ካጋሜ ግን የአሜሪካንም ሆነ የሌሎች አገራትን መሰል ጥያቄ፣ በምስራቅ አፍሪካ አገራት የውስጥ ጉዳዮች ላይ የሚደረግ ጣልቃ ገብነት ነው ሲሉ ማጣጣላቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡
አጃንስ ፍራስ ፕሬስ በበኩሉ÷ የህገ መንግስት ማሻሻያው በመጪው ሳምንት በሚደረገው ህዝበ ውሳኔ ድጋፍ አግኝቶ የመጽደቅ ዕድሉ ከፍተኛ ነው ሲል ዘግቧል፡፡

Read 1479 times
Administrator

Latest from Administrator