Saturday, 28 November 2015 14:21

“Roots” የስዕል ኤግዚቢሽን አርብ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

   15 የሚደርሱ ዕውቅ ሰዓሊያን የሚሳተፉበት “Roots” የተሰኘ የስዕል አውደ ርዕይ የፊታችን አርብ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በላፍቶ አርት ጋለሪ እንደሚከፈት ተገለፀ። በአውደ ርዕዩ ላይ ታዋቂዎቹ ሰዓሊያን ታደሰ መስፍን፣ መዝገቡ ተሰማ፣ ወርቁ ማሞ፣ ጌታቸው ዮሴፍ፣ ኑሩ አበጋዝ፣ ሰይፉ አበበ፣ ሜሪኮከብ ብርሃኑ፣ ስዩም አያሌው፣ ዳንኤል አስፋው፣ ተከሰተ ይበይን፣ ሚካኤል ፀጋዬ፣ ሰለሞን ተሾመ፣ ሳምሶን መረሳ እና ደረጄ ደምሴ በሴቶች ህይወትና አካባቢ ላይ የሚያጠነጥኑ የቀለም ቅቦች፣ ቅርፃ ቅርጽና የፎቶግራፍ ስራዎቻቸውን ለዕይታ ያቀርባሉ ተብሏል። ላፍቶ አርት ጋለሪና ኦክስፋም በመተባበር የሚያዘጋጁት ይሄ የስዕል አውደርዕይ፤ ለአንድ ወር ለተመልካች ክፍት ሆኖ ይቆያል ተብሏል፡፡

Read 1856 times