Saturday, 28 November 2015 14:19

የሳቅ ንጉስ በላቸው ግርማ በጀርመን በሦስት ውድድሮች ሪከርድ ሰበረ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(4 votes)

   የዓለም የሳቅ ንጉስና የደግነትና የመልካም ሥነ - ምግባር አምባሳደር በላቸው ግርማ፣ በጀርመን በርሊን ከተማ “ኢምፖሲቢሊቲ ቻሌንጀር 2015” ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ በሶስት ውድድሮች ሪከርድ መስበሩን ባለፈው ረቡዕ በተገን ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡ ከውድድሮቹም አንዱ ቀድሞ በ3 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ተመዝግቦ የነበረውን ዓለም አቀፍ የሳቅ ሪከርድ 3 ሰዓት ከ35 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ በመሳቅ በሰፊ ልዩነት ያሻሻለ ሲሆን በሚሄድ መኪና ጣሪያ (ፖርቶመጋላ) ላይ በጭንቅላቱ ቆሞ ለአንድ ደቂቃ ከ40 ሰከንድ 86 ሜትር በመጓዝ ሪከርድ መስበሩንም ጨምሮ ገልጿል፡፡
በላቸው መለከት በመንፋት በተካሄደው ውድድር 3 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ ያለማቋረጥ መለከት በመንፋቱ አዲስ ሪከርድ መስበሩን ጠቁሞ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን የእውቅና ሽልማት ለጋዜጠኞች አሳይቷል፡፡ የማይቻሉ ነገሮችን በመሞከር ዘንድሮ በርካታ አዳዲስ ነገሮች እንደተመዘገቡ የገለፀው የሳቅ ንጉስ፤እሱም ከሚታወቅበት የሳቅ ውድድር አልፎ በሁለት አዳዲስ ውድድሮች ሪከርድ በመስበር አገሩን ለዓለም ማስተዋወቁ እንዳስደሰተው ተናግሯል፡፡  

Read 5040 times