Saturday, 21 November 2015 13:42

“ዋልያ” የንግድ ምልክት ሄኒከንንና ካንጋሮን እያወዛገበ ነው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(5 votes)

   የዋሊያ ቢራ አምራቹ ሀይንከን ብሪወሪስ አክሲዮን ማህበርና ካንጋሮ ፕላስት ኃላደነቱ/የተ/የግል ማህበር በንግድ ምልክትና ስያሜ እየተወዛገቡ ነው፡፡
በካንጋሮ ፕላስት በ2003 ዓ.ም የተያዘው የአይቤክስ የንግድ ምልክት ለ3 ዓመት ያለአገልግሎት መቀመጡን የጠቀሰው ሃይንከን ብሪወሪስ፤ ዋልያ እና አይቤክስ የተለያዩ እንስሳት ናቸው ሲል የዋልያ ምልክት ብቸኛ ባለቤት መሆኑን አስታውቆ ነበር - ባለፈው ሳምንት በተለያዩ የፕሬስ ውጤቶች ባወጣው ማስታወቂያ ካንጋሮ ፕላስት በበኩሉ፤ ምልክቱን በተመለከተ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ፅ/ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃወም ለከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ ጠይቆ ፍ/ቤቱ የንግድ ምልክቱንና ስያሜውን እንደወሰነለት አስታውቋል፡፡
“ድርጅታችን ቀደም ብሎ በጥናትና በጥንቃቄ መርጦ ለአገራችን ገበያ እጅግ ተስማሚና ትርፋማም ያደርገኛል ብሎ የመረጠውንና በአዕምሯዊ ንብረት ያስመዘገበውን የአይቤክስ ምልክት ሀይንከን ያለአግባብ ተጠቅሞበታል” ያለው ካንጋሮ፤ ፍ/ቤት ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ “ሄኒከን እኔ ነኝ ህጋዊ ባለቤት ብሎ መግለጫ ማውጣቱ ተገቢ አይደለም” ሲል ተቃውሟል፡፡
የዋልያ የንግድ ምልክት ህጋዊ ባለቤት ሄኒከን ብቻ መሆኑን በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ አስመዝግበን አስመስክረናል የሚሉት የሄኒከን የኮርፖሬት ሪሌሽን ማኔጀር ወ/ሮ ሠራዊት በዛብህ፤ እነሱ የሚሉት አይቤክስ ነው፤ አይቤክስና ዋሊያ ደግሞ ፈፅሞ የተለያዩ ናቸው፤ ፈፅሞ አይገናኙም ብለዋል፡፡
“በፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔም ስለ አይቤክስ እንጂ ስለዋሊያ የሚገልፅ አይደለም” ብለዋል ወ/ሮ ሠራዊት፡፡


Read 4229 times