Print this page
Saturday, 11 February 2012 09:33

ብሉ ናይል “አፍሪካ አቀፍ የፊልም አውደ ርእይ” አዘጋጀ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ብሉናይል የፊልምና ቴሌቪዥን አካዳሚ አፍሪካ አቀፍ የፊልም አውደ ርእይ አዘጋጀ፡፡ በመጪው ሕዳር 2005 ዓ.ም ይቀርባል ተብሎየሚጠበቀውን አውደርእይ ድርጅቱ ያዘጋጀው ከኢትዮጵያ የፊልም ሰሪዎች ማህበር ጋር በመተባበር ነው፡፡ “ከለርስ ኦፍ ዘ ናይል አለምአቀፍየፊልምፌስቲቫል” በሚል መጠርያ የተቋቋመውና በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው አውደርእይ አፍሪካዊ ፊልምችን በዓለም አቀፍ መድረክ የማስተዋወቅ ዓላማ ያለው ሲሆን የሚካሄደው አዲስ አበባ ውስጥ ነው፡፡ የፌስቲቫሉ ፕሬዚዳንትና የብሉናይል ፊልምና ቴሌቪዥን አካዳሚ መሥራች ሲኒማቶግራፈር አብርሃም ኃይሌ ብሩ ስለዚሁ ሲናገሩ፤ “የአውደርእዩ ተቀዳሚ አላማ የአፍሪካን ሲኒማ እና ፊልም ገበያ ማጠናከር እና የልምድ ልውውጥ መድረኮችን መፍጠርና ማስፋፋት እንዲሁም ሥልጠና መስጠትና የሲኒማ ጥበብን ማስተዋወቅ ነው፡፡ ወጣት ፊልም ሠሪዎችን እናበረታታለን” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፊልም ሰሪዎች ማህበር ፕሬዚዳንት ረዳት ፕሮፌሰር ሃይማኖት ዓለሙ በበኩላቸው፤ ለአንድ ፊልም አውደርእይ ቀጣይነት ተቋማዊ አደረጃጀቱ ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስ ብሉ ናይል ፊልም እና ቴሌቪዥን አካዳሚን አድንቀዋል፡፡ የፈረንሳይ አምባሳደር የአውደ ርዕዩን መጀመር አስመልክቶ ባቀረቡት ግብዣላይለአዲስአድማስለዚሁሲናገሩ“አንድየቻድፊልምአይቼበፎቶግራፊው ከተደመምኩበኋላይህንየሰራውአብርሃምመሆኑንሳውቅአፈላልጌአገኘሁት፤በሥራው ስለተማመንኩም ለአውደ ርእዩና ለአካዳሚው ድጋፍ እያሰባሰብኩ ነው” ብለዋል

 

 

 

Read 1160 times Last modified on Saturday, 11 February 2012 09:35