Saturday, 11 February 2012 09:07

ቦኖ የ”ምንጊዜም ሃብታም ሮክ ስታር” ተባለ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

የዩ2 የሙዚቃ ባንድ መሪ አቀንቃኝ ቦኖ ባስመዘገበው 1.2 ቢሊዮን ዶላር ሃብት “የምንጊዜም ሃብታም ሮክ ስታር” መባሉን አይሪሽ ታይምስ ዘገበ፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት 90 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት በማድረግ የፌስ ቡክ ኩባንያ ባለድርሻ የሆነው ቦኖ፤ ዘንድሮበኩባንያውየ1.5በመቶባለቤትነት ይዟል፡፡ ይሄው የቦኖ ድርሻ የዋጋ ተመን 1 ቢሊዮን ዶላር መሆኑንም አይሪሽ ታይምስ አመልክቷል፡፡ ፌስ ቡክ 100 ቢሊዮን ዶላር የሚያንቀሳቅስና በዓለም ዙርያ 850 ሚሊዮን ደንበኞች ያሉት ኩባንያ ሲሆን 1 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ ትርፍ ያገኛል፡፡

ለቦኖ ሃብት መጨመር በፌስቡክኢንቨስትመንት ማድረጉ አስተዋፅኦ ቢኖረውም በዋናነት ከዩ2 ጋር ያቀረበው “360 ዲግሪ” የተሰኘ የሙዚቃ ዝግጅት ለገቢው መጨመር ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ ቡድኑ ባዘጋጀው ለሦስት ዓመት የዘለቀ የሙዚቃ ትርኢት 7 ሚሊዮን ተመልካች በማግኘት 705 ሚሊዮን ዶላር ማስገባቱ ይታወቃል፡፡

 

 

 

Read 1212 times Last modified on Saturday, 11 February 2012 09:10