Saturday, 03 October 2015 10:26

ሸራተን 7፣ ራዲሰን ብሉ 5 ሆቴሎችን በአፍሪካ ሊከፍቱ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሰሞኑን አዲስ አበባ ውስጥ እየተካሄደ ባለው የ2015 የአፍሪካ ሆቴሎች ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ የሸራተን ሆቴሎች ባለቤት ኩባንያ የሆነው ስታር ውድ ሆቴል እና ሪዞርትን ጨምሮ ራዲሰን ብሉ፣ ሞቪንፒክ ሆቴል እና የስብሰባ ማዕከል እንዲሁም ሌሎች ዝነኛ አለማቀፍ ሆቴሎች በአፍሪካ ሆቴሎችንና ሪዞርቶችን ለመገንባት ስምምነት ፈጽመዋል፡፡የሸራተን መለያ ስም ባለቤት የሆነው ስታርውድ ኩባንያ፤ በ5 የአፍሪካ ሀገሮች ተጨማሪ 7 ሆቴሎችን ለመክፈት ተስማምቷል፡፡
በግብፅ፣ በማሊ፣ በናይጄሪያ 2፣ በኬንያ፣ በሴኔጋል ሆቴሎቹ በመጪው አመት ይከፈታሉ ተብሏል፡፡ ራዲሰን ብሉ ሆቴልና ማረፊያ በበኩሉ፤ በአሁን ወቅት ኢትዮጵያን ጨምሮ በ27 የአፍሪካ ሀገራት 65 ሆቴሎችን እንደሚያስተዳድር ጠቁሞ በዚህ አመት መጨረሻ በኬንያ እና በሌሎች 5 የአፍሪካ ሀገራት አዳዲስ ሆቴሎች እንደሚከፍት አስታውቋል፡፡
 በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆቴል ስራውን በናይጄሪያ ለመጀመር ማቀዱን የጠቆመው ሞቪንፒክ ሆቴልና የስብሰባ ማዕከል በ4 አመት ውስጥ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የሚችል ሆቴል እገነባለሁ ብሏል፡፡ከናይጀሪያ ቀጥሎ በሞሮኮም ሆቴል መገንባቱን እንደሚቀጥል ጠቁሟል፡፡

Read 1863 times