ፍቺ በአንድ ሺ ፐርሰንት እንኳ ቢጨምር በሴቶች የመብት እንቅስቃሴ የተነሳ ነው እንዳትሉ፡፡ ተጠያቂው ትዳሮቻችን የተመሰረቱበት ጊዜው ያለፈበት የፆታ ሚናችን ነው፡፡
ቤቲ ፍሬይዳን
(አሜሪካዊ ፀሐፊ)
የሴት የሥራ ሙያ፣ በተለይ ስኬታማ ከሆነ በተደጋጋሚ ለትዳር መፍረስ በምክንያትነት ይቀርባል፡፡ የወንዱ ግን ጨርሶ ተነስቶ አያውቅም፡፡
ኢቫ ቪጌስ
(እንግሊዛዊ ፀሐፊ)
የፈሪ ሚስት ከመሆን ጀግና ባልዋ የሞተባት ሴት መሆን ይሻላል፡፡
ዶሎሬስ ኢባሩሪ
(የስፓኒሽ ፖለቲከኛና ጋዜጠኛ)
ጄን ኦስተንስ፣ ጆርጅ ኒሊዬትስ እና ሮዛ ቦንኸርሰን ብትሆኚና ሳታገቢ ብትቀሪ ምንም ፋይዳ አይኖረውም ነበር፡፡ ከተሰጥኦ ይልቅ ባል ይሻላል፡፡
ጆርጅ ሙር
(የአይሪሽ ፀሐፊ)
አፍቃሪ ሚስትን፤ ባሏ ላይ ትችት ከመሰንዘርና ህይወቱን ለማሻሻል ከምታደርገው ጥረት ታቀቢ አይበሏት እንጂ ሌላ ምንም ነገር ቢሆን ታደርግለታለች፡፡
ጄ.ቢ.ፕሪስትሌይ
(እንግሊዛዊ ፀሐፊ)
ሚስት የሌለው ወንድ ልጓም እንደሌለው ፈረስ ነው፡፡
የቬትናሞች ምሳሌያዊ አባባል
ሚስት የምትፈለገው ለመልካም ባህርይዋ ነው፡፡ ውሽማ ደግሞ ለውበትዋ፡፡
የቻይናውያን አባባል