Friday, 11 September 2015 09:28

ዘመን ተቀየረ እላለሁ

Written by  ነ.መ
Rate this item
(17 votes)

አበባ አዙሬ አዙሬ
ዘመን በዘመን ቀይሬ
ትላንትን በዛሬ አስሬ
ነገን ሰርቼ ተሻግሬ
የአበባ እድሜዬን አብስዬ
ይኸው አብቅቼው ለፍሬ
ፍላቴን በስክነት ሽሬ
ለሰው ከሰው በሰው ውዬ
እኔኑ ከኔው ፈጥሬ!
የእድሜ እንቁጣጣሽ
ቅጥልጥል ችቦ አበራለሁ ዛሬ!
ዘመን ተቀየረ እላለሁ
እኔ ራሴ ተቀይሬ!
ይህ ነው የለውጥ ነውጤ፣ የለሆሳሴ ዝማሬ
ደሞ ለላመት ልፈትል፣ የልደቴን ነጭ ሸማ
ነፍሴ እንዳታድር ከርማ
በውሃ ቀለም አጥባለሁ
ነፍሴን እንደ አበባ አዙሬ
ለምን ተቀየረ እላለሁ፣ እኔ እራሴ ተቀይሬ!
(ለ 2008 እንቁጣጣሽ )

Read 3708 times