በዚሁ መሠረት ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካዊ ሙዚቀኛ ነገ ከቀኑ 11፡30 በጃዝ ክለብ አብሮት ከመጣው ቡድን ጋር ሥራዎቹን የሚያቀርብ ሲሆን ረቡዕ ምሽት በአሜሪካ ኤምባሲ “Music As a Business” የሚል የክብ ጠረጴዛ ውይይትም ይካሄዳል ተብሏል፡፡ በምሽቱ ደግሞ በጣይቱ ሆቴል እና በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት መሠል ዝግጅቶች ይኖራሉ፡፡ በሌላ በኩል “ሕይወት እዚህ ቦታ” የተሰኘ የግጥምና ሙዚቃ ዝግጅት ዛሬ ማታ በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ይቀርባል፡፡ ዝግጅቱ አሜሪካ ሀገር ከሚገኘው ጣይቱ ባህል ማዕከል ጋር በመተባበር ተቀርፆ እዚያው ሀገር በሚገኝ ሬዲዮ ጣቢያ እንደሚተላለፍም ታውቋል፡፡ ከገጣሚዎቹ መካከል ኤፍሬም ስዩም፣ ሰለሞን ሳህለ፣ ዮሐንስ ሐብተማርያም ይገኙበታል፡፡