Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 04 February 2012 12:28

የሊያም ኔሰን ‹ዘ ግሬይ› ወጣ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በቦክስ ሳምንታዊ የገቢ ደረጃ ሰሞኑን አንደኛ ደረጃ የያዘው ሊያም ኔሰን በመሪ ተዋናይነት የተሳተፈበት “ዘ ግሬይ” ሲሆን በሰሜን አሜሪካ 24.7 ሚሊዮን ዶላር አስገኝቷል፡፡ ፊልሙ ሰው ከተፈጥሮ ጋር የሚያደርገውን ትንቅንቅ የሚተርክ ፊልም ነው፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ 12 አዳዲስ ፊልሞች ለእይታ የበቁ ሲሆን ገቢያቸው ባለፈው አመት በተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 40 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡በ2012 የመጀመርያ ወር የሆሊውድ ፊልሞች ገቢ 831 ሚሊዮን ዶላር እንደተመዘገበ ያመለከተው ቦክስ ኦፊስ ሞጆ፤ ይህ የገቢ መጠን ከአምናው በ10 በመቶ ያነሰ መሆኑን ገልጿል፡፡ የወሩን ከፍተኛ ገቢ ያስመዘገበው ደግሞ የቶም ክሩዝ “ሚሽን ኢምፖሲብል ጎስት ፕሮቶኮል” ሲሆን 80.7 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱ ታውቋል፡፡

 

 

Read 1516 times Last modified on Saturday, 04 February 2012 12:31