Print this page
Monday, 31 August 2015 09:05

ሙዚቃን በከፍተኛ ድምፅ ማዳመጥ ለመስማት ችግር ይዳርጋል ተባለ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ metijossy@gmail.com
Rate this item
(2 votes)

    ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ በመጡ የMP3 የሙዚቃ ማጫወቻዎች ሙዚቃዎችን በከፍተኛ ድምፅ አዘውትሮ ማዳመጥ ቋሚ ለሆነ የመስማት ችግር እንደሚዳርግ ጥናቶች አረጋገጡ፡፡በቅርቡ የተደረጉ ጥናቶችን ዋቢ አድርጐ “ኢንተርናሽናል ሔራልድ ትሪቢዩን” እንደዘገበው፤ በሳምንት ቢያንስ ለአምስት ሰዓታት ያህል በከፍተኛ የድምፅ መጠን ሙዚቃ የሚያዳምጡ ሰዎች ቋሚ ለሆነ የመስማት ችግር ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡ በጆሮ ማዳመጫዎች ተጠቅመው ሙዚቃን በከፍተኛ ድምፅ ረዘም ላሉ ሰዓታት የሚያዳምጡ ሰዎች እድሜያቸው ሃያዎቹን ከማገባደዱ በፊት የመስማት ችሎታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ ጥናቱ ማረጋገጡን ጋዜጣው ዘግቧል፡፡ሙዚቃን በከፍተኛ ድምፅ በተንቀሳቃሽ ሙዚቃ ማዳመጫዎች መስማት ጉዳት የሚያስከትለው ወዲያውኑ ሳይሆን በቀጣይ አመታት ውስጥ እንደሆነ በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡የ115 ዴሲቤል መጠን ያለው ድምፅ በሚያወጣ የሙዚቃ ማጫወቻ በቀን ለሃያ ስምንት ሰከንዶች ብቻ ሙዚቃ ማዳመጥ በጊዜ ሂደት የመስማት ችሎታን እንደሚያሳጣም ጋዜጣው ጥናቱን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

Read 4650 times