Print this page
Saturday, 04 February 2012 12:26

ካናን ሚት ሮምኒን ተቃወመ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ሶማሊያዊው ድምፃዊ ካናን ‹ዌቪንግ ዘፍላግ› በተሰኘው ታዋቂ ዘፈኑ ለአሜሪካ ፕሬዝዳንት ምርጫ ሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው የሚወዳደሩት ሚት ሮምኒ ለቅስቀሳ መጠቀማቸውን እንዳወገዘ ኒውዮርክ ታይምስ አስታወቀ፡፡ ሚት ሮምኒ ባለፈው ሰሞን የሪፐብሊካን ፓርቲን በመወከል በፕሬዝዳንት እጩ ሆነው ለመቅረብ ባደረጉት ቅስቀሳ የካናንን “ዌቪንግ ፍላግ” በማጀቢያ ሙዚቃነት ተጠቅመዋል፡፡ ካናን በጉዳዩ ላይ ባወጣው ኦፊሴላዊ መግለጫ፤ ዘፈኑን ለመጠቀም ምንም አይነት ፈቃድ አለመጠየቁ እንዳሳዘነው ገልፆ ቢጠየቅ እንኳን ፈቃዱን ለመስጠት ፍላጎት እንደሌለው ተናግሯል፡፡ ካናን የዲሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው በፕሬዝዳንትነት እየሰሩ ያሉት ባራክ ኦባማ፤ ዘፈኔን ለምርጫ ዘመቻ መጠቀም ከፈለጉ ግን ደስተኛ ነኝ ብሏል፡፡ የካናን “ዌቪንግ ዘ ፍላግ” ዜማ በደቡብ አፍሪካ ተደርጎ በነበረው 19ኛው ዓለም ዋንጫ ጋር በተያያዘ የዓለም አቀፍ ተወዳጅነት ያተረፈ ሲሆን በብዙ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ተዘፍኗል፡

Read 1225 times