Print this page
Saturday, 28 January 2012 13:58

በ“ሬድ ኤፒክ” ካሜራ ፊልም ሊሰራ ነው

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(0 votes)

ሮዛ ፊልም ፕሮዳክሽን በአዲስ ፕሮጀክት ከአሜሪካ በመጡ ኢትዮጵያውያንና አሜሪካውያን ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በመታገዝ የመጨረሻው የካሜራ ቴክኖሎጂ ነው ባለው “ሬድ ኤፒክ” ካሜራ ፊልም ሊሰራ መሆኑን ገለፀ፡፡ የፕሮዳክሽኑ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል በየነ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት “Still I am a Virgin” የሚል ጊዜያዊ የእንግሊዝኛ ርእስ የተሰጠው የአማርኛ የፍቅር ፊልም እና “አላስታውስም” የአሳዛኝ ታሪክ ፊልም ቀረፃ ከመጋቢት 1 ጀምሮ በጐንደር፣ በአዲስ አበባ፣ በመቀሌና፣ መተማ ይከናወናል፡፡ ለዚሁ ተግባር የሚያስፈልጉ 300 ተዋንያንና ተሳታፊዎች ለማዘጋጀት ምልመላው ከነገ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ይከናወናል፡፡ ሮዛ ፊልም ፕሮዳክሽን ካሁን ቀደም “መንታ ነፍስ” የሚል ፊልም የሰራ ሲሆን አሁን እየታየ ያለውን “ሹገር ማሚ” ፊልም ለዕይታ አብቅቷል፡፡

 

 

Read 1202 times Last modified on Saturday, 28 January 2012 14:04