በያዝነው የፈረንጆች አመት በርካታ ሰራተኞችን ቀጥረው እያሰሩ ከሚገኙ የዓለማችን ተቋማትና ድርጅቶች መካከል፣ 3.2 ሚሊዮን ሰራተኞችን የሚያስተዳድረው የአሜሪካ መከላከያ ሚንስቴር ፔንታገን በሠራተኞች ብዛት መሪነቱን መያዙን ፎርብስ መጽሄት ዘገበ፡፡
የአለም የኢኮኖሚ ፎረም ሰሞኑን ይፋ ያደረገውን የጥናት ውጤት ጠቅሶ ፎርብስ ባለፈው ማክሰኞ እንዳስነበበው፣ የቻይና ህዝቦች የነጻነት ጦር 2.3 ሚሊዮን ሰራተኞችን በመያዝ በሁለተኝነት ሲከተል፣ ታዋቂው አለማቀፍ የሸቀጣሸቀጥ ሱፕርማርኬት ዎልማርት በ2.1 ሚሊዮን ሰራተኞች ሶስተኛውን ደረጃ ይዟል፡፡ በአመቱ በርካታ ሰራተኞችን በስሩ ቀጥሮ በማስተዳደር ከአለማችን አራተኛውን ደረጃ የያዘው ደግሞ 1.9 ሚሊዮን ሰራተኞች ያሉት ታዋቂው የምግብ አምራች ኩባንያ ማክዶናልድ ነው፡፡
የእንግሊዝ ብሄራዊ የጤና አገልግሎት ድርጅት በ1፣7 ሚሊዮን ሰራተኞች አምስተኛ ደረጃን እንደያዘ የገለጸው ዘገባው፣ የቻይና ብሄራዊ የነዳጅ ኮርፖሬሽን በ1.6 ሚሊዮን፣ የቻይናው ስቴት ግሪድ ኮርፖሬሽን በ1.5 ሚሊዮን፣ የህንድ ምድር ባቡር ኩባንያ በ1.4 ሚሊዮን፣ የህንድ የጦር ሃይል በ1.3 ሚሊዮን እንዲሁም ሆን ሃይ ፕሪሲዥን የተባለው ኩባንያ በ1.2 ሚሊዮን ሰራተኞች እስከ አስረኛ ደረጃ ይዘዋል ብሏል፡፡
Published in
ከአለም ዙሪያ
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል