የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ና 17ኛ ወንጀል ችሎት ባለው ሰኞ እና ማክሰኞ በዋለው ችሎት የቅጂና ተዛማጅ መብቶች የጣሱ ግለሰቦችን በእስር ቀጣ፡፡ በዚሁ መሠረት ማርታ እንግዳወርቅና ብዙአየሁ ኩሽ እያንዳንዳቸው 2 ዓመትና በ3 ወራት ጽኑ እስራት፣ ተቀጥተዋል በተመሳሳይ ወንጀል ክስ የቀረበባቸው አስናቀ ተመስገን በሦስት ዓመት ጽኑ እስራት፣ አበበ ዘውዴ አምስት ዓመት ከ4 ወር ተቀጥተዋል፡፡ በግለሰቦቹ ላይ ውሳኔው የተላለፈው ነሐሴ 21/2003 ዓ.ም በመላ ኢትዮጵያ በተደረገው የፍትህ ሚኒስቴር፣ ፌደራል ፖሊስና የክልሎች ፖሊስ ፍተሻ የቅጂና ተዛማጅ መብቶች በመጣሳቸው ነው፡፡