Saturday, 20 June 2015 11:43

“የፊልም ዝግጅት ቴክኒክና ጥበብ” ተመረቀ

Written by 
Rate this item
(5 votes)

በፊልም ጥበብ ባለሙያው ሰለሞን በቀለ ወያ የተዘጋጀው “የፊልም ዝግጅት ቴክኒክና ጥበብ” 1ኛ መፅሃፍ በትላንትናው ዕለት በጀርመን ባህል ተቋም (ገተ ኢንስቲቲዩት) ተመርቋል፡፡
መፅሃፉ በፊልም አሰራር፣ ቴክኒካዊ ጥበብና በፊልም አዘገጃጀት ዙሪያ የቀረበ ትምህርታዊ መፅሃፍ ሲሆን ደራሲው በዘርፉ የካበተ የማስተማር ልምድ ያላቸው መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ደራሲው በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር ዩኒቨርሲቲዎች ከፊልምና ከስነፅሁፍ ጋር የተያያዙ ትምህርቶችን በተለያዩ የዲግሪ ደረጃዎች የተማሩ ሲሆን ታዋቂ በሆኑ አለማቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይም በዳኝነት መስራታቸው ተገልጿል፡፡
ባለሙያው ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ጥናታዊ ፊልሞችን የሰሩ ሲሆን በሀገሪቱ የመጀመሪያው እንደሆነ የሚነገርለትን “አስቴር” የተሰኘውን ባለ 35 ሚ.ሜ ልብ ወለድ ፊልም በደራሲነት እና በዳይሬክተርነት አዘጋጅቶ በማቅረብና በሲኒማ ቤቶች ለረጅም ጊዜያት እንዲታይ በማድረግም ውጤታማ ስራ መስራታቸው ተጠቅሷል፡፡
በአሁን ሰዓት ደራሲው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሂውማኒቲስ ኮሌጅ የውጭ ቋንቋዎች ክፍል በዘመናዊ የአውሮፓ ቋንቋዎች ዩኒት ውስጥ በማስተማር ላይ የሚገኙ ሲሆን የተለያዩ የፊልም ጥበብ ስልጠናዎችን እንደሚሰጡም ታውቋል፡፡

Read 2855 times