የሰዓሊ ግዛቸው ከበደ 20 የሚደርሱ የስዕል ሥራዎች ለዕይታ የሚቀርቡበት ኤግዚቢሽን በትላንትናው ዕለት ምሽት ከገርጂ መብራት ኃይል ወደ ሳሊተ ምህረት በሚወስደው መንገድ፣ ከሮቤራ ካፌ ጀርባ፣ በማላንጋ የስዕል ጋለሪ ተከፈተ፡፡ ኤግዚቢሽኑ ለተመልካች ክፍት የሚሆነው ዘወትር ቅዳሜና እሁድ፣ ለአራት ተከታታይ ሳምንታት ነው ተብሏል፡፡ ሰዓሊው የአሁኑን ጨምሮ በ50 የስዕል ኤግዚቢሽኖች ላይ (በግልና በቡድን) ሥራዎቹን እንዳቀረበ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሰዓሊና ቀራጺ ግዛቸው ከበደ፤ ከዚህ ቀደም ዘመን ባንክ በር ላይ የቆመውንና በአሜሪካ የስቶክ ገበያ ተምሳሌት የሆነውን የበሬ ኮርማ (bull) ፣ከፊትለፊቱ በኦዳ ታወር ላይ ያለውን ሞሳይክ መስራቱ የሚታወቅ ሲሆን ስቴዲየም በሚገኘው የኦሮምያ ባህል ማዕከል ባለ ሁለት አውታረ መጠን ቅርጾችንም ሰርቷል፡፡
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና