Saturday, 28 January 2012 13:41

ሴሊና የሙዚቃ ስራዋን አቆመች

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ወጣቷ ድምፃዊና የፊልም ተዋናይት ሴሊና ጎሜዝ የሙዚቃ ስራዋን በማቆም በፊልሞች ትወና ላይ ማተኮር እንደምትፈልግ ኢንተርቴይመንት ዊክሊ አስታወቀ፡፡ ዘንድሮ ለገበያ ይቀርባል ተብሎ የተጠበቀው አራተኛው አልበሟም ወደ ቀጣዩ ዓመት እንደተሸጋገረ ተገልጿል፡፡ዓመቱን በሁለት ፊልም ስራዎች ላይ እንደምታሳልፍ የገለፀችው ሴሊና ጎሜዝ፤ የሙዚቃ አልበሟን ከዚያ በኋላ ቀስ ብላ መስራት እንደምትፈልግ ገልፃለች፡፡ አርቲስቷ ከፍቅረኛዋ ከጀስቲን ቢበር ጋር በመጣመር በምትወዳቸው ሁለት ሙዚቃዎቹ ላይ የመስራት እቅድ እንዳላትም ተናግራለች፡፡ ሴሊና “ዘ ስካይ ኢዝ ኤቭሪዌር” በተሰኘ ፊልም ላይ በተዋናይነትና በፕሮዲውሰርነት እንደምትሰራ የተገለፀ ሲሆን ፍቅረኛዋ ካናዳዊው ጀስቲን ቢበርም በፊልሙ ላይ ይሳተፋል ተብሏል፡፡ “13 ሪዝንስ ዋይ” እና “ሆት ሜስ” የተሰኙ ኮሜዲ ፊልሞች ሴሊና በዚሁ ዓመት የምትሰራቸው ናቸው፡፡በዲዚኒ ቻናል በምትሰራባቸው የቴሌቭዥን ፊልሞች በአማካይ እስከ 4 ሚሊዮን ተመልካች ያላት የ19 ዓመቷ ሴሊና፤ በታዳጊነታቸው ከተሳካላቸው አርቲስቶች ተርታ የምትጠቀስ ናት፡፡ “ድሪም አውት ላውድ” በተባለ የፋሽን ልብሶች መደብሯ ባለፈው ዓመት ትርፋማ የሆነችው አርቲስቷ፤ 100 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንዳገኘች ታውቋል፡፡

 

 

Read 1499 times Last modified on Saturday, 28 January 2012 13:44